It’s for orthodox Christians so what exactly is Emnet not the faith or belief but the one that is taken from the church (like ash, soil)? And what is the purpose or use? Please explain this in detail
Oct 22, 2023.........መላእክቱ ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት እንዲታሰቡለት ነው፡፡ በኢሳ. 56፣4-6 ባለው ምንባብ ላይ ‹‹ደስ የሚያሰኝ ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣችኋላሁ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣ ቸዋለሁ፡፡›› ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት እዚህ ላይ ጃንደረባ የሚለው ቃል በማቴ፡19-12 ስለመንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን ጀንዳረቦች ያደረጉ አሉ በማለት የዚህን ዓለም ፍትወቱን፣ ፍቅርን ሁሉ ትተው መስቀሉን ተሸክመው በብቸኝነት ራሳቸውን ያሳለ ፋትን ቅዱሳኑን መሆኑን ያረጋግጣል ለቅዱሳኑ " ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ" ማቴ10፥8 በማለት ስልጣን ሰጧቸዋል በተጨ ማሪም የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ነው፡፡ መታሰቢያቸውም ለበረከት ነው፡፡ መዝ፡111-7 ምሳሌ 10-7 በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በጠበሉ ቅዱሳኑ መጠራታቸው መታሰቢያቸው እንዲሆን ነው፡፡ መታሰቢያቸው ብቻ ሳይሆን በረከትም አለው ብለን እናምናለን እንጂ ጠበሉን ያፈለቀው መድኃኔዓለም አምላካችን ኢየሱስ ክር ስቶስ መሆኑን በጠበሉም አድሮ ሕሙማንን የሚፈ ውሰውና ተአምራትም የሚያደርገው ሁሉን ቻይ የሆነው የ እግዚአብሔር ኃይል መሆኑ ጠፍቶብን አይደለምና በጸበሉ ታጥበን እንድንፈወስ የሆነው በሚታይ በሚጨበጠው ቅዱሳት ምልክቶች የማይ ታዩትን የማይጨበጡትን አጋንንትን በማባረር ሕሙማንን የመፈወስ ተአምራትን የማድረግ ረቂቅ ኃይሉን እንዲአስተላላፍባቸው ስለፈቀደ ነው ለምሳሌ ያህል፡፡ የኤርትራን ባሕር የመክፈል ኃይሉን በሙሴ በትር ዘፀ/14፣15-16 ሙት የማስነሳት ኃይሉን በአጽመ ኤልሳዕ 2ኛ ነገሥ 13-20 ደዌያትን የመፈወስ ኃይልን በቅዱስ ዘይት ማር 6፡14 ያዕ፡5-14 አጋንንትን የማባረር ኃይሉን በቅ/ጳውሎስ ልብስ የሐዋ. 19-11 እንዳስተላለፈ ሁሉ በዚህ ጸበል ተብሎ በተጠራው በቅዱስ ውሃም እስከአሁን ድረስ ወደፊትም ሕሙማንን የመፈወስ ታም ራትን የማድረግ ረቂቅ ኃይሉን እያስተላለፈልን እየተፈወስን እንገኛለን፡፡ ወደፊትም እንፈወሳለን፡፡ “ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፣ እናንተም ትጠራላችሁ ከርኲሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ፡፡” ሕዝ.36፥25 "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" ማር 16፥
Oct 23, 2023