✅ግራአዝማች በግራ በኩል የሚያዘምት ✅ቀኝአዝማች በቀኝ በኩል የሚያዘምት(ሁለቱ ማለትም ግራና ቀኝ ባሁኑ ዘመን ክፍለ ጦር እንደምንለው ማለት ናቸው) እና እንደሰማሁት እና እንዳነበብኩት ብዙም ማንበብ ባልወድም ቀኝ ግራን ያዘዋል ይባላል እርግጠኛ ግን አይደለሁም፡፡ ✅ደጅ አዝማች የግራና ቀኝ የበላይ ራንክ ነው ፡፡ ሙሉ ክፍለጦር ይይዛል ባስ ሲል ካስፈለገ ወቶ ሌላ ድንበር የማዋጋት ብቃት አለው ✅ፊት አውራሪ ከፊት ሆኖ ከግራም ከቀኝም ከኋላ ደጀንም ያሉትን እያሰባጠረ የጠላትን መሃል ለመሃል እየሰነጠቀ የሚያተራምስ (እንደፊት አውራሪ ደፋር እና ጀግና አይገኝም ✅ባላምባራስ/ ራስ - ይህ ማእረግ የሚሰጠው ከንጉሱ ቀጥሎ የማዘዝ ስልጣን ላለው ሰው ነው። ባላምባራስ ማለት የአንባው ራስ ወይም የአንድ ክፍለሃገር መሪ ማለት ነው በጦርነት ግዜ ንጉሱ ክተት ሲጠሩ የሁሉም ጦር አዛዦች የበላይ አዛዥ ሆኖ ይዟቸው ይመጣል ከሱ ስር ያሉት አዛዦች እሱ እሚሰጣቸውን ትእዛዝ ይቀበላሉ።
Oct 18, 2023