Orthodox ወንድም እና እህቶች በሕይወቴ ትልቅ የሆነ ውድቀት ገጥሞኛል መቋቋም አቃተኝ ምን ላድርግ።
Oct 16, 2023እመን አንተ ከውድቀትህ መነሳት እንደምትችል ፀሎት አድርግ አልቅስ ይቅርታን ጠይቅ አምላክህን ቤተ ክርስቲያን ሂድ ንሰሐ አባትህን አግኝ እርሳቸውን አናግር። ለራስህ ይቅርታ አድርግ
Oct 17, 2023Orthodox ወንድም እና እህቶች በሕይወቴ ትልቅ የሆነ ውድቀት ገጥሞኛል መቋቋም አቃተኝ ምን ላድርግ።
Oct 16, 2023እመን አንተ ከውድቀትህ መነሳት እንደምትችል ፀሎት አድርግ አልቅስ ይቅርታን ጠይቅ አምላክህን ቤተ ክርስቲያን ሂድ ንሰሐ አባትህን አግኝ እርሳቸውን አናግር። ለራስህ ይቅርታ አድርግ
Oct 17, 2023እግዚአብሔር ይስጥልኝ አመሠግናለሁ
Oct 17, 2023እግዚአብሔር ሁልጊዜ ወደ መከራ እንዳትገባ አያደርግም። አንዳንድ ጊዜ በወጀብ ውስጥ መንገድ ያዘጋጅልሃል። ግፊው በሚበዛበት ዐውሎ ነፋስ እያለፍህ ተፍገምግመህ እንዳትወድቅ ጉልበትህን ያጸናል፤ ኃይልን ያስታጥቅሃል። እንዲህ እያደረገ በመንፈስ ያጎለምስሃል። እግዚአብሔር ዳንኤልን በአናባስት ጉድጓድ ከመጣል፣ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት ከመግባት፣ ጳውሎስና ሲላስን ወደ ወኅኒ ከመውረድ ሊያድናቸው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ እንዲህ አላደረገም። አምላካችን ፈተና ካለባቸው ቦታዎች ሁሉ ሊያወጣን ቃል አልገባምና። ነገር ግን በመከራ ጊዜያችን ሁሉ ከእኛ እንደማይለይና በእውነት ይዘነውም እንደ ሆነ በድል ነሺነት እናጠናቅቅ ዘንድ እንደሚረዳን ቃሉን ሰጥቶናል። የጌታ እናት እመቤታችን የተወደደ ልጇን ይዛ በግብጽ በረሃ እንደ ወፍ ከተንከራተተች በኋላ ሕፃኑን የሚፈልገው ክፉ ሄሮድስ ሲሞት ተመልሳ ወደ ገሊላ ገብታለች። እንደ ድንግል ጌታን በመሐል እጅህ ብትታቀፍ እንኳን ግብጽ መውረድ አይቀርልህም። ይሁን እንጂ የመጣብህን መከራ ድል ነሥተህ ወደ ገሊላ መመለስህም እርግጥ ነው። "ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" 1ኛ ቆሮ 10፥13 ዲያቆን አቤል ካሳሁን I hope this will help mewedk sewawi bahri wedko mekeret gn aydelem repent egeziabher hulunm yastekakelal ayzon hulum yalfal!
Oct 17, 2023እመን እንጂ አትፍራ። ሰውን ከትቢያ ላይ የሚያነሳ ይቅር ባይ አምላክ አለክ : እሱን አትርሳ። ዘወተር ፀልይ👏 ከንስሃ አባትክ ጋር ተነጋገር በግልፅ። አንድ ጊዜ አውጥተህ ከተናገርክ በኋላ እና ንስሃ ከተቀበልክ ሸክም የሆነብክ ሁሉ ነገር የት እንደ ሄደ አታውቀውም። ጌታ ከአንተ ጋ እንዲሆን እፀልያለሁ። አሜን! ሃሌ ሉያ!
Oct 17, 2023እግዚአብሔር ይስጥልኝ አመሠግናለሁ
Oct 17, 2023ወደ ኢየሱስ ቅረብ, ለጥያቄያችን ሁሉ መልስ እርሱ ነውና.
Oct 17, 2023