እርዳታቹ ያስፈልገኛል ምን መሰላቹ ከፍቅረኛዬ ጋር ከተለያየን 1ወር አልፎናል ምክንያቱም እኔ ነበርኩ ግዜ አልሰጣትም ነበር ግን ከልቤ ይቅርታ ጠይቂያት አብረን እንድንሆን ብዙ ጊዜ ለመንኳት ምንም ልትቀበለኝ አልፈለገችም ብዙ ነገር አሳልፈናል እኔ ደግሞ እሷን መርሳት አቃተኝ ለሷ በጣም ጥሩ ሰው ነበርኩኝ ግን እንዴት ባንዴ እንዴት ልትወስን ቻለች የመጀመሪያዬ ናት pls ሴቶች መልሱልኝ........ከምርም ግን ሴቶች ክብር ሚሰጣቹን ሚጨነቅላቹን ወንድ አትፈልጉም ካልተቀበለችኝ በጣም መጥፎ ሰው እንደምሆንባት እየተሰማኝ ነው ምን ልወሰን ሀሳባቹን አጋሩኝ
Oct 15, 2023ምታፈቅራት ከነበረ ጊዜ ልትሰጣት ይገባ ነበር ሲቀጥል አሁንም ቢሆን አወራርህ ከEGO የፀዳህ እንዳልሆንክ ያሳያል ፍቅር ደሞ መቻቻል መተናነስ ነው ጥሩ ሰው ነበርኩ ላልከው ፍቅር እና ጥሩነት ለየቅል ናቸው በውለታ ልታስራት ማሰብህ ተገቢ አልነበረም ወደ ዋናው ሀሳብ ስንመጣ ጊዜ ስላልሰጠሀት እና አንተ እራስህን የተሻልኩ ነኝ አይነት Attitude ስላሳየሀት ቀድማ እሷም ሳታስበው subconsciously ተዘጋጅታበት ነበር ማለት ነው ብዙ ጊዜ ወንዶች ማንረዳው ነገር ይቅርታ ስላልን ነገሩን የፈታነው ይመስለናል አንድ ቀን ዘግተሀት ስታድር ካንተ ውጪ ያለውን ህይወት እያለማመድካት መሆኑን አስብ የመጨረሻ ምክር መጥፎ ሰው ብትሆን ራስህን ነው ምትጎዳው የተሻለው ጥሩ ነገር ለደስታዋ ተዋት እሷ ትወስን አንተ እንዳልከው ጥሩ ሰው ከነበርክ በሷ ህይወት ውስጥ ራሷ ትመጣለች ካልሆነም ምርጫዋን አክብር final tip እየለመንካት ወይም እያስፈራራሀት በሄድክ ቁጥር ይበልጡኑ እየጠላችህ ነው ምትሄደው
Oct 16, 2023