Selam Endet nachu Bahunu G12 yetefetenachu wetetachehun endet acyachehut? From your side? From Friends, Family side? Lene le next year felegew nw Thank you
Oct 15, 2023Man ልምከርህ ዝም ብለህ አጥና በቃ እራስህን ከአዳሪ እና ከግል ተማሪዎች Level አብቃ 1.አቅድ ለምሳሌ ዛሬ ያለፈ ክላስ ምከልስ ከሆነ እቅድ አውጣ ምሳሌ : 9 ነኛ ክፍል Math አንድ የሆነ Chapter.. Cover ለማድረግ አቅድ በየሳምንቱ ወይም በየ5ቀኑ እቅድህን መገምገም መከለስ 2.የራስህ የሆነ የጥናት ስታይል ቢኖርህ ይህን ስልህ ግን ከእንቅልፍ ከጤና ከውጤት አንፃር አይተህ ቢሆን ጥሩ ነው የሌላም ሰው ስታይል ቢሆን ከጠቀመህ ውሰደው ለምሳሌ አንድ ጓደኛዬ ከክላስ እንደወጣ Nap ይወስዳል ከዛ እስከ ለሊት 8 ያጠናል ከዛ ተመልሶ ይተኛል ፣ ሌላኛው ጓደኛዬ ደግሞ ከክላስ እንደወጣ በዛው ያጠናል ግን እስከ 6 ነው የሚያመሸው አንዳንዶች ደግሞ ለሊት ይነሳሉ... በቃ ብቻ የጥናት የሕይወት ዘይቤ ልምድህ አድርግ 3. በቡድን የማጥናት ልምድ ይኑርህ ይህ ለማስታወስ በጣም ይረዳሃል ሁለት ሶስት ጓደኞችህ ጋር ሆነህ በቃ ጥያቄ ፍለጡ ፣ አጥኑ ... 4.ስልክህን ወይም ሶሻል ሚዲያን ለእውቀት ተጠቀመው Workbook ስራበት ፣ Ethio Matric ...Exam Veda ... ይህን ላንተ አልነግርህም ያው ስልክህን ሌላ ወሬ ምናምን ላይ ሳታበዛ ለእውቀት ተጠቀም 5. አትሸበር ፡ በትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ዜናዎች ፣ በሀሰተኛ መረጃዎች ፣ በተደጋጋሚ ሞዴሎች አትሸበር አትደንግጥ ፈተና ሲደጋገም በጣም ይጠቅማል እና ደግሞ ሁሌም ዝግጁ ሁን ነገ ኢንትራንስ ነው ብትባል እራሱ ለመፈተን የሚያበቃ Confidence እና አቅም ይኑርህ ሞዴሎች ደግሞ ሲሰረቁ ቀድመህ አትስራ ራቅ አውቃለሁ ከተያዘ ውጤትህን እንደሚያወርደው ግን አንተ በደንብ ካጠናህ ፈቀቅ አትልም ሌላው 6.ከማንኛውም ሱስ ራቅ 7. Consistent ሁን ከላይ ያልኩህን ነገሮች አታቋርጥ በቀጥታ ለረጅም ጊዜ የማድረግ ልምድ ይኑርህ በመጨረሻም እግዚአብሔር ይርዳህ ያው እኔ አዳሪ ነው የተማርኩት እና የጠቀሙኝ እና ደግሞ Consistency ቢኖረኝ ካሁኑ የተሻለ ውጤት ላመጣ የምችልበትን ነገሮች ነው የነገርኩህ። እና ካንተ ቢያንስ ከ 630 በላይ እጠብቃለሁ በርታ🙌
Oct 15, 2023