እኔ እምላችሁ ግን በ90ዎቹ መጀመሪያ የተወለድን ሰዎች ግን የሆነ ሁለት ትውልድ መሀል የተሰነቀርን አይመስላችሁም? ስርአት ነው አይደለም እያልን ነገሮችን ለመለየት ምንጋጋጠው እኛ ብቻ እንደሆንን ይሰማኛል ስታስቡት እስኪ በምን መስፈርት ነው እኔ ከታናሽ ወንድሜ በተሻለ ቤተሰብ ምፈራው? ታናናሾቻችን በሚያወሩት ወሬ ምንሳቀቀው እኛ ብቻ እንደሆንን አስባችሁታል? ደሞ የሆነ የዚህ ትውልድ አካል ነን ለማለት ይሁን ቦታችን ጠፍቶን በማይታወቅ መልኩ ራሳችንን የሆነ የኛ በማይመስል ነገር ውስጥ ከተነው ስንኳትን ምንኖር ትውልዶች እንደሆንን ሚሰማኝ እኔን ብቻ ነው? ትምህርት ህልም ሰርቶ መለወጥ ስነስርዓት ሚባሉ ነገሮች እኛ መዝገበ ቃላት ላይ የከሰሙ ያህል ሚሰማኝ እኔን ብቻ ነው ወይስ እናንተንም ነው?
Oct 15, 2023በስተመጨረሻም ራሴን ሌላ ሰው ውስጥ አገኘሁት 😢
Oct 15, 2023