ሰላም። እኔ ምለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዩኒቨርሲቲ ከሆነ አይሰረቅም ተብሎ ከታሰበ ፈተናው እዚያው ሆኖ ተማሪዎች እየተመላለሱ ቢፈተኑ ችግሩ ምንድነው? እኔ ለምሳሌ የ2015 ተፈታኝ ነበርኩኝና ስድስት ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነበር የደረሰኝ እናም በደንብ ለመዘጋጀት ሁሉንም መፅሐፎቼን ይዤ ነበር የሄድኩት። ነገር ግን ምንም ሳልከፍት ነው የተመለስኩት ምክንያቱም ቀን ቀን ምግብ ፍለጋ እንዞራለን በቀላሉ ስለማይገኝ ማታ ማታ ደግሞ HORROR የሆነ ሀይለኛ እረብሻ አለ(ተማሪዎች ይጮሀሉ፣ ማብራቱን ያጠፉታል፣ ድንገት ደግሞ ፌደራሎች ይመጡና ካልተኛቹ ይዘዋቹ ይሄዳሉ)። ነገር ግን እረብሻው ብዙም አይቆይም ቢበዛ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከንጋቱ 1 ሰዓት ቢቆይ ነው😂ቀልድ እንዳይመስላችሁ የምሬን ነው እንኳን ማጥናት ማሰብም አትችሉም። እኔ ለመውደቄ ምክንያት እየደረደርኩ ሳይሆን እውነቱን ነው የምናገረው ምክንያቱም አልፊያለው (የጠበኩትን ባላገኝም)። ቤቴ ብሆን ግን የበለጠ ተዘጋጅቼና ተረጋግቼ እሰራው ነበር ብዬ አስባለሁና ከቤት ወደ ዩኒቨርስቲ እየተመላለስን ብንፈተን ችግሩ ምንድነው?
Oct 14, 2023Abdellaaaaaaaaa 😂😂😂😂 I remember Minm altegnanm neber
Oct 15, 2023