ሰላም እንዴት ናቹ👋 ምን መሠላችሁ የ2014 ተፈታኝ ነበርኩ እና ያኔ በግል ኮሌጅ remedial መጣልኝ እና ተምሬ አለፍኩ ይመስገን 🙏ግን በመሀል ፈተናው ሲቋረጥ private ሞልቼ entrance ድጋሚ ተፈተንኩ እና አሁን ያመጣሁት 261 ነው በኛ ጊዜ የመንግስት ዩንቨርስቲ ለ remedial የሚያስገባ ነበር እና ዩንቨርስቲ መግባትም ሰለምፈልግ ነበር private የተፈተንኩት medicinal ለማጥናት ማለትም ነው ♧በ remedial ውጤቴ Degree ልማር ወይስ በ private ዩንቨርስቲ ገብቼ Remedial ደግሜ ልማር ግራ ገባኝ እኮ እኔ 1 medicinal መማር ፈልጋለሁ 2 በግል ኮሌጅ ክፍያው ብዙ ነው 3 በአከባቢ ያሉ ሰዎች ከሰው ጋር እያነፃፀሩ ሰላም ነሱኝ ምን ላርግ ? ልሂድ remedial ወይስ ልቅር ለ degree ሚዛናዊ የሆነና በቦታው እንደሆናችሁ አርጋችሁ ምላሽ ስጡኝ አመሰግናለሁ
Oct 12, 2023አርፈህ ድግሪ ተማር ግቢ ገብተህ remedial ላታልፍ ትችላለህ... ካለፍክ ደግሞ medicine coc ከባድ ነዉ እሱንም ላታልፍ ትችላለህ.... ካለፍክ ደግሞ medicine ተምረው ሚጨርሱ ጥቂት ናቸው 5ተኛ አመት ላይ intern ፈተና አለ እሱንም ሚወድቁ ነፍ ናቸው ካለፍክ ይሄን ሁሉንም ደግሞ ስራ ወፍ የለም.... ስራ ካገኘህ ደግሞ ደሞዝ ቢበዛ 8000,9000 ነዉ በዚህ ኑሮ አስበው ስራው አናትህ ላይ ይወጣል ደሞዝህ ግን እንደያዝከው ይበተናል አርፈህ ድግሪህን ተማር ጎን ለጎን ስራህን ስራ ይሄ ህዝብ ሃብታም ሆነህ በመኪና ካልመጣህለት በቀር ሰላም አይሰጥህም ሁሌም ከንፈር ነዉ ሚመጠው ዶክተር መሆንህን እንጂ ደሞዝህን እና ችግርህን አያውቁም ኤኬሌ ዶክተር ነዉ እያለህ በየመንገዱ ሲያገኝህ ብር ቡና መግዣ ብር እንድሰጠው ይጠብቃል ከዛች ደሞዝህ ሚቀበልህ እንጂ ሚጨምርልህ ወፍ የዛን ጊዜ ትነቅላለህ ምነው ባልተማርኩ ትላለህ ... ደሞ እጮኛ ትመጣለች ቤተሰብ ካንተ ይጠብቃል ወዳጄ አንድ ነገር ልንገርህ የት እንደ ምትመደብ ራሱ አታውቅም... ከምትኖርበት ዉጪ ከሆነ ቤት ክራይ, ምግብ, ብቻውን ያስጨልልሀል.... አሁን ምርጫህን አስተካክል ለማህበረሰብ ሳይሆን ለራስህ ኑር ነገ ስታገባ ይሄ ማህበረሰብ አብሮ ኑሮህን አይገፋልህም... ከሟሽሟጠጥ በቀር ዛሬ ምርጫህን አስተካክል ::
Oct 13, 2023