ማንብ ያለብኝ ነገር ካለ mention አድርጉኝ ወይም ደግሞ አስረዱኝ እግዚአብሔር ሲፈጥረን ነፃ ፈቃድ ሰቶናል በነፃ ፈቃድ እና በተፃፈልን እጣፈንታ መካከል ያለውን ልዩነት በዝርዝር አስረዱኝ ለቀና ትብብራችሁ ከልብ አመሠግናለሁ
Oct 08, 2023እግዚአብሔር ነጻ ፈቃድ ሰጥቶናል አዎ ልክ ነው። ግን የተጻፈልን የሚባል ነገር የለም እግዚአብሔር ቀድሞ የምናደርገውን ያውቃል ማለት ተጽፎልናል ማለት አይደለም። ሁሉን ነገር እንድናደርግ ፍቃድ አለን( እጅህን ወደ ውሀም፣ እሳትም ማስገባት ትችላለህ እንደሚለው መጽሐፍ ቅዱስ) የምናረጋቸውን ነገሮች እግዚአብሔር ቀድሞ ያውቃል ታዲያ መጥፎ ነገር ልናረግ ስንል ለምን አያስቆመንም ብንል:- ቢያስቆመን ኖሮ ነጻ ፍቃድ አለን ብለን መናገር አንችልም። ስለዚህ ሁሉ ነገር ለማረግ ነጻ ፍቃድ አለን እነዛን ነገር እንደምናደርግም እርሱ ያውቃል። ያውቃል ማለት ደግሞ ተጽፏል እሱን ለመተወን ነው እዚህ አለም የመጣነው ማለት አይደለም
Oct 09, 2023