ሰላም AAE Medicine የመግባት ትልቅ ፍላጎት ነበረኝ፣ ማለት ቤተሰብ ምናምን ገፋፍቶኝ ሳይሆን የእውነት ፍላጎት ነው ያለኝ። እናም entrance ላይ 555 ነው ያመጣሁት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ ግን ሁኔታዎች እንደጠበኩት ስላልነበረ EiABC(urban planning) field ደረሰኝ። እሱንም እሺ ብየ 1 ሴሚስተር ተማርኩኝ ግን አልሆነም grade 2.00 ሁላ ለማምጣት እየተቸገርኩ ነው። እና ምን ትመክሩኛላቹ? አሁን እኔ እያሰብኩ ያለሁት withdraw አድርጌ ድጌ entrance ተፈትኜ ሜድ መግባት ነው።
Oct 07, 2023እኔም እንዳንተ medicine መግባት እያሰብኩ መጨረሻ ላይ Engineering ደረሰኝ። አለም ዞረብኝ…AAU ስለነበርኩ EiABC ተፈተንኩ። ፈተናዉን ሳየዉ በቃ Arch ለኔ አይሆንም ብዬ ፈተና አበላሽቼ ወጣሁ። ከዛ በራሳቸዉ Chemical engineering ከተቱኝ። ላይፍ ተመሰቃቀለ…ሰቃይ የነበርኩት ልጅ Probation እና warrning ላይ ወደቅኩ። መዉጣት አልችልም ኮሌጅ ከፍዬ መማር አልችልም ነበር። ስለዚህ ሳልወድ በግዴ ዉስጤን አሳምኜ ቀን ከለሊት እያጠናሁ ግሬዴ ከሞተበት እየተነሳ መጥቶ በ2.8 አጠናቀቁት። ቀጣይ ጉዞ ስራ ሆነ። ስራዉን ጠላሁት ጠላሁት…አሳድጄ 15 ቀን ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ስራ አገኛለሁ ግን ፍላጎት ስለሌለኝ ጥዬዉ እወጣለሁ። 5 አመት ትምህርት ከዛ በኋላ 7 አመት አባክኜ ከ12 አመት በኋላ medicine የመማሪያ ሞራል ስለሌለኝ ሌላ Hobby ስለነበሩኝ photography And fashion Design ተማርኩ። ወደድኩት ስማራቸዉም ደስ ብሎኝ ስሰራቸዉም ደስ ብሎኝ ነዉ አሁን። Am 30 now…ምን ልልህ ነዉ ዉስጥህ ያልወደደዉ ነገር ላይ ጊዜ አታጥፋ። እንደኔ እድሜህን አስጨርሶህ ዉጤት አልባ ነዉ የሚያረግህ። እኔ የሚመክረኝ ስላልነበር ነዉ 12 አመቴን የሰዋሁት። አስብበት!! የምትፈልገዉ medicine ትምህርት ብር የለዉም አሁን ላይ ምትፈልገዉ ከሆነ ግን አማራጮች አይጠፉም ወደኋላ ተመልሰህም ቢሆን ወይም ኮሌጅ ተማረዉ። የሚወደዉን ነገር የተማረ ስኬታማ ነዉ።
Oct 08, 2023