ቤተሰብ እንዴት ናችሁ እስኪ እናንተ ጋር መፍትሄ አይጠፋም ብዬ ነዉ መላ በሉ ምን መሰላችሁ የሴት ጓደኛ አለችኝ ከተዋወቅን አንድ አመት ልሞላን ነዉ በጣም ቀይራኛለች ለዉጣኛለች even እሷን ከተዋወኩኝ ወዲህ ከእራስን ማርካት (ሴጋ) ሱስ ወጥቻለሁ ይሄ ብቻ አይደለም በጣም ብዙ ነገር እሷም በጣም ጥሩ ልጅ ናት ነገር ግን እስካሁን ፍቅር አልጀመርንም ግን በደንብ እንዋደዳለን ፍቅርም ማይቀር ነገር ነዉ ወሬ አላብዛችሁና ወደ ጉዳዬ ልግባ ከእኔ ጋር ከመተዋወቋ በፊት ፍቅረኛ ነበራት እኔ ስተዋወቃት ተለያይተዉ ነበር ነገር እንዲህ ትለኛለች "ለእኔ በህይወቴ ሁለት ሰዉ ብቻ ናቸው የራሴ ምላቸዉ አንደኛው አንተ ነህ ሁለተኛዉ ብላ ያንን ልጅ ትጠራለች"...በጣም እናደዳለሁ ግን አልነግራትም ይባስ ብሎ ስልክ ይደዋወላሉ ከአንድ ሰዓት በላይ ያወራሉ ሌላዉ ደሞ ባለፈዉ አገኘችዉ በድጋሚ ትናንት ከልጁ ጋር እና ከልጁ ወንድ ጓደኛ ጋር አብረዉ ነዉ ያመሹት ደሞ ሁሉንም ነገር ትነግረኛለች አትደብቀኝም እኔ ደግሞ በቶሎ እናደዳለሁ ራስምታት ሊገለኝ ይደርሳል ሳላዉቅ አስቀይማታለሀ ብዬ እራሴን በደንብ እቆጣጠራለሁ ኦንላይን እያወራን ከሆነ ስልኬን እወረዉራለሁ ቶሎ ወጣለሁ። ከእኔ ማንንም እንደማታስበልጥ አዉቃለሁ ነገር ግን ይሄ ትክክል ነዉ ብዬ አላምንም እና ምን ላድርግ እባካችሁ መፍትሄ ስጡኝ። አመሰግናለሁ።
Oct 01, 2023ነገ ሌላ ነገር ያመጣል አንተም ስሜትህን ደስ እንደማይልህ ንገራት ሌላው እንደ ፍቅረኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ባልም ተቆጣት... ሌላው በጣም ታፈቅራታለህ እድለኛ እንደሆነችም ንገራት 🥰
Oct 01, 2023