ሰዎች አትለፉኝ ኦርቶዶክሶች ምን መሰላችሁ ፍቅረኛ ነበረኝ የሌላ እምነት ተከታይ ነው እና ብዙ ግዜ ግንኙነት አርገናል ከዛ ከሌላ አምነት ጋር ግንኙነት ያረገ 7 አመት ቤተክርስቲያን አይገባም የሚል ነገር ሰማው እና እባካቹ እውነት ነው ይሄ። ሁተኛው ጥያቄዬ ደሞ እውነት ከሆነስ በምን ማስተካከል ችላለው ማለት ንሰሀ ብገባ ይሰረዝልኛል🙏 በቅንነት መልሱልኝ ሳትቀልዱ
Sep 27, 20231. መጀመሪያ ላይ መልስ የሰጠሽን ባለጌ ብሎክ አድርጊው። መዳን የሚጀምረው ከክፉ መካሪ ዓይንንም ጆሮንም ከመጠበቅ ነው። 2. ውሸት ነው። ሰባት ዓመት ቤተክርስቲያን አይግባ የሚል ሕግ የለም። ከቀድሞ ቤተክርስቲያን ሐኪም ቤት ናት። በኃጢአት የታመምን እኛ ስንሄድባት ደግሞ በሽተኞች ናችኹና አትምጡ አትግቡ አትልም። ንስሐ ግቡ እንጂ። ከዛም በቀኖናሽ መሰረት የታዘዘልሽን መፈጸም። ኋላም ቄደር መጠመቅ ነው። ቤተክርስቲያን አትቅሪ ከደጇ ወድቀሽ ግን ምሕረት ለምኚ። 3. ከዚኽ ሰው በፍጥነት ተላያይ።
Sep 27, 2023