በሕይወቴ ተስፋ የቆረጥኩበት ግዜ ላይ እገኛለሁ የነካሁት ሁሉ ይበላሻል ለእናቴ ሸክም የሆንኩ ሰው ነኝ ምን እንደማደርግ አላውቅም እስኪ የሆነ ነገር በሉኝ ምንም ስኬታማ መሆን አልቻልኩም በጣም ጨንቆኛል ለቀና ትብብራችሁ ❤️🙏
Sep 25, 2023የመጀመሪያዉ ማድረግ ያለብሽ ነገር ፀሎት ነዉ። እኛ ሰዎች ሁሌ እንድናስብ የተደረግነዉ ስኬት ማለት ምቾት እንደሆነ ነዉ። ስኬቱ ላይ ያለዉን ዉጣ ዉረድ ማን ወስዶልን ነዉ ምቾቱ ጋር ከመጀመሪያ ጀምሮ ልንደርሶ የምንችለዉ? መዉበቅ፣መነሳት፣ መላልሶ መዉደቅን መልመድ አለብን። በዚህ ሰዓት በዙሪያችን ያሉ ሁሉ ከሰሩ ሊሉን ይችላሉ። አላማዉን እና ግቡን የሚያዉቅ ሰዉ ግን በዚህ አይረበሽም። ጉልበቱን ሰብስቦ ይቀጥላል። እኔ የት ትደርሳለች የተባልኩ ሴት ስንቴ የህይወትን ፈተና እንደወደቅኩ አጠይቀኝ። በት/ት፣በስራ፣ በፍቅር ጉዳይ ብቻ የምታወቀዉ በመሞከርና በመዉደቅ ነዉ። አይደክማትም እስክባል ድረስ። ለካ እግዚያብሄር ትልቅ ነገር ሊሰጠኝ አስቦ ትችለዋለች ወይ ብሎ ከጋግሞ በነገሮች እያስተካከለኝ ነበር ለካ። እ/ር የለም አያየኝም ብዬም አዉቃለሁ። አሁን እንዴቴ በትልቅ ደስታ እና ስኬት እንደባረከኝ ልነግርሽ አልችልም። እግዚያብሄር ያያል! የሚክስ አምላክ ነዉ። ተስፋ መቁረጥ የሚባለዉን ነገር ትተሽ ተጋፈጪዉ። ለሁሉም ቀን አለዉ።
Sep 26, 2023