Selam tewedajoch ... የዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ ይህችን አመት ተወኝ mezmur getem felge nbr kalachu lakulegn urgent nw pls...
Sep 14, 2023ይህችን አመት ተወኝ ከዓመት እስከ ዓመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለበ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እንዳጎሳቆልኩኝ አውቃለሁ አምላኬ ፍሬን ለመቀበል እንዳመላለስኩህ ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅዬ ደርቄ ጠበቅሁህ ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አለየኝም ካለም የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ የኔን ክፋት ተወው መልዐክህን ሰምተህ ይህችን ዓመት ተወኝ አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር ብዙ ጊዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይሄን ጊዜ ሰምተኸኝ ነበረ ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮዬ አልፎ በአዲስ ተቀየረ ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጥያት መታመሙ የቃልህን ውሃ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳትታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ ወደ ልቤ ሳይሰርግ ሕይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈስሶ ቀረ ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ ብዙ ጥቅስ አገኘው ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ በበደል ተኝቼ ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርጸኝ ተማሪ ብሆንም ይህችን ዓመት ተወኝ ደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መዓዛ እንዲደርሰኝ የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሸከመኝ አትሰልቸኝ አደራ ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት አይሰሩ ስሰራ አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ ቦታስ የሚይዙት ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸው ልክ እንደ ዘንባባ የተንዘረገገ ተጋድሎ ጽድቃቸው ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው እኔ አይደለሁም ቦታስ የምትይዘው ያንተስ እናት ናት ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት ይህችን ዓመት ተወኝ ከስሯ እሆናለሁ ባፈራ ምናልባት ይህችን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት ሺህ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንት ናት ይሄ ዓመት አልፎ ዳግም ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ እባክህን ጌታ ይህችን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ አዲስ የበገና መዝሙር ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
Sep 15, 2023