ከቦሌ ክፍለ ከተማ ህንፃ ፊት ለፊት ከመገናኛ - ወደ ቂሊንጦ ኮንዶሚንየም የሚያመላልሱ አንበሳ ባሶች አሉ። የ10 ብር ትራንስፖርት ነው። የመጨረሻው ፌርማታ ከመድረስህ በፊት ባንክ በመባል ከሚታወቀው መዞሪያ ሳትደርስ በዩኒቨርሲቲው በር ትይዩ ትወርዳለህ። (ዩኒቨርሲቲው ከምትወርድበት መንገድ ባሻገር ነው ሚገኘው።) የታክሲ አማራጭም አለው። ከቦሌ ክፍለ ከተማ ህንፃ ፊትለፊት ከመገናኛ ኮዬ ፈጬ የሚያመላልሱ ታክሲዎች አሉ። ኮዬ ፈጬ አደባባዩ ላይ ትወርዳለህ። የ30 ብር ትራንስፖርት ነው። ከዚያ ከወረድክበት ቦታ ብዙም ሳይርቅ ባንክና ታች ሰፈር ወደሚባል ቦታ የሚያደርሱ ባጃጆች ታገኛለህ። ባንክ ጋር ሳትደርስ ዩኒቨርሲቲው ጋር ትወርዳለህ። የ5 ብር ትራንስፖርት ነው።
Sep 14, 2023