Hey guys Wede gudaye Sgeba btm mafekrew sew nbr like bttm gn bzu gize enchekachek nbr mlt chla endemilegn ysemagnal ena chla mtlgn eyemeselegn new mnamn eyalku btm echekeckew nbr ene endemhonlet endemayhonlgn awkalew bzu tukret efelgalew kesu esu gn Yann lisetegg alchalem... Enam yehone ken betam eyetechekachekn slk tezega kza bezaw tefa sdewl be sreat liyawerag fkadega alnbr zm alkut kza belela ken lay btm midebr ngr tenageregn ena lben seberew bka bttm tesemag kza ykrta biteykegnm ene gn wste likebelew alchalem mn larg
Sep 12, 2023ስለ የፍቅር ቋንቋችሁ ያለመተዋወቅ ችግር ይመስለኛል። አንቺ ማበድ ማቀፍ የፍቅር ቃላት መደርደር ሊመችሽ ይችላል። እሱ ደግሞ ካከበርኳት፣ከጋበዝኳት፣ ካወራን በቂ ነዉ ሊል ይችላል አዉሩበት። ያፈቀረ ሰዉ ማድረግ የሚችለዉ መስጠት ብቻ ነዉ። ያ ሰዉ ጋር ተመሳሳይ ነገር ሲፈጠር ይመልሰዉ ይሆናል በሌላ መንገድ ስለዚህ ተመሳሳይ መልስም ሆነ ሌላ መልስ ከባለቤቱ እስኪመጣ መታገስ ጥሩ ነዉ። ሴቶች ብዙ ግዜ ይሄን ያንን እንፈልጋለን እያልን መናገር የለብንም አስመሳይ ወንድ እሱን አድርጎ ህይወታችንን ያመሳቅለዋል። ዝም ብለን አታዘብ የምንፈልገዉን ነገር በተፈጥሮዉ የማያረገዉ ከሆነ መተዉ ወይንም ለመለወጥ በጣም ብዙ ጊዜ ስለሚወስድ መታገስ። የምትፋቀሩ ከሆነ ተነጋገሩበት ቂም አትያዙ እርሱት። እድሜያችን አጭር ነዉ በጭቅጭቅ እና በቂም ማለፍ የለበትም። አንቺም ድምፅሽን ዝቅ አድርገሽ በትህትና አዉሪዉ። ሴት ብልጥ ከሆነች ማንኛዉንም ወንድ የራሷ ማረግ ትችላለች። አክብሪዉ፣አፍቅሪዉ፣ አለም ብጥብጥ አርጋዉ አንቺ ጋር የሚመጣዉ ለማረፍ ነዉና ሰላም ስጭዉ። እኛ ሴቶችን የሚያባብለን የሚረዳን ብዙ ሰዉ አለ። ለወንዶች ግን ብቸኛዋ ልትኖር የምትችለዉ ሚስቱ ወይም ፍቅረኛዉ ናት። ስለዚህ ታገሺዉ። ሴጣን ፍቅርን አይወድም እና ለሱ አትሸነፊ። መለስ በይ፣!
Sep 13, 2023