ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ አንድ ጥያቄ ነበረኝ ፍቅረኛየ ጋር በቅረቡ ነው አብረን ማደር የጀመርነው ስለ sex ላወራ አይደለም ለሊት ላይ አብረን ተኝተን በጣም ነው ምታስፈራው አንዳንዴ ምንነቱ ያልታወቀ ቋንቋ ታወራለች አንዳንዴ ትጮሀለች ወይ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች አንዳንዴ ተነስታ ቁማ እኔን ዝም ብላ ታፈጥብኛለች ከሁሉ ሚያስደነግጠኝ ግን አይኗን ገልጣ እንኳ ሰኒየ መጣሽ እየጠበኩሽ ነበር እያለች ከሰኒ ጋር ታወራለች ሰናይት ማናት ስላት በሌላ ቀን ሰናይት ምትባል ልጅ አላውቅም ትለኛለች ስለዚህ ጉዳይ ላወራት ስፈልግ ታስቆመኛለች ምትወደኝ ከሆነ አታንሳብኝ ብላ ታለቅሳለች ፀበል እንድትጠመቅ አሳምኛት ነበር ግን አሁን ላይ እረፍት ስለላት ከመስከረም በኋላ ብላኛለች ምን ላድርግ ጨነቀኝ እኮ
Sep 10, 2023ይሄ ከባድ ሰይጣን እና ቅዥት ነው እና ከቻልክ 21 ቀን ወይም ሁለት 7 አፀብላት መፅሐፍ ቅዱስ, ውዳሴ ማርያም,ቀ ትርሃስ ስር አድርጋችሁ ተኙ ፀበል ግን ግድ ነው ጥዋት ጥዋት ደሞ ፀበል አጠጣት.. 🙏🙏🙏
Sep 11, 2023