DuskParrot26108.5
#other
Hi የኔ ጥያቄ ለመብራት ሃይል ሰራተኞች ነው። እናም ጥያቄዬ የብዙ(የድፍን) ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው ብዬ አስባለሁና እዛ መስሪያቤት ካሉ ከጥበቃና ፅዳት ጀምሮ ዘና ብለው ተቀምጠው ኦንና ኦፍ እስከሚያደርጉት ድረስ ካላችሁ እናንተ መስሪያቤት ምን እየተካሄደ እንዳለ እንድትነግሩኝ በጥብቅ እፈልጋለሁ። ከሌሉ ደግሞ እዛ የሚሰራ ዘመድ ያላቹ ካላችሁ ተባበሩኝ።ቆይ ሲበላሽ ነው የምናጠፋው(የሚቋረጠው) ካላችሁ እንዴት ነው በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት rhythm እየጠበቀ የሚበላሸው ወይስ እኛ ሳናውቅ ተዓምር እየተፈጠረ ነው? ሲቀጥል ደግሞ ሲበላሽ ለምንድነው አፋጣኝ ምላሽ የማትሰጡት? ያው ባሁን ጊዜ ያለመብራት ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይከብዳል(አይቻልም)። እኛ ያልተረዳነው አስቸጋሪ የሆነባችሁ ነገር ካለ ደግሞ ንገሩንና እንረጋጋ። Thanks
Sep 10, 20232 engagements