ሰላም።ምን መሠላችሁ ዛሬ የእናቴን መኪና ይዤ ወደ ሸገር ሄጄ ነበርና ደንብ አስከባሪዎች በየቦታው አስፓልት ዳር ቆመው ነበር።ከዛም በሰላም እየነዳው እያለ አንዱ(ደንብ አስከባሪው) ለመሄድ እንደሚፈልግ ሰው በእጁ ምልክት ሲያሳየኝ እኔ ደግሞ ማንንም እንዳትጭን ተብሎ ከባድ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠኝ በምልክት እዚሁ አካባቢ ነኝ እያልኩኝ መኪናውን አቆምኩት።ከዛም ሰውየው የሆነ ነገር በኦሮምኛ ተናገረ እኔ ደግሞ ቋንቋውን ስለማልችል ምን አልከኝ ብዬ ጠየኩት። ከዛም ተናዶ እጅህን ለምንድነው የጠቆምከው ብሎ በተበሳጨ ፊት ጠየቀኝ እኔም ይቅርታ እንድጭንህ የጠየከኝ መስሎኝ እዚሁነኝ ለማለት ፈልጌ ነው ስለው እንደገና የበለጠ ተናዶ እያንቋሸሸኝ እና ቢሆንስ ወደህ ነው የምታቆመው ''ጭልፋ ፊት'' ጥፋ ከዚህ ሲለኝ መንፈሴ ከስጋዬ ተለየች፣ሰማይና ምድሩ ተደበላለቀብኝ የሆነ የማይረባ ክብረቢስ እንደሆንኩ ተሰማኝ።እውነት ለመናገር ስድቡ አጥንቴን🦴ነክቶት ነበር እኔ ደግሞ በዚያ ሰዓት ምንም ማድረግ አለመቻሌን ሳስብ በጣም ተናደድኩኝ።ንግግራችንን ቃል በቃል ምን ሳላስተካክል ነው የፃፍኩት።ንቀቱን፣ማመናጨቁንና ማንቋሸሹን ብታዩ።እናም ጥያቄዬ እንደዚህ አይነት አለመግባባት ሲፈጠር ሁልጊዜም መሸነፍ ልክ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?በዛ ሰዓት ምን ማድረግ እችል ነበር?እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር?አሁን እናቴን እንደዛ ተናግሯት ቢሆን ትልቅ ችግር ይፈጠር ነበር።
Sep 06, 2023እንደተማረ ሰው ትክክል ነዉ ያረከው, እንደ ወንድ ግን መልስ መስጠት ነበረብህ ግን ምን ያረጋል ጊዜው የ ደንብ አስከባሪዎች ነዉ ☺️
Sep 06, 2023