እናንተ በኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ? የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ ታናሾች አሉኝ እናም ለፍታ ጥራ የምታሳድገን ውድ እናት አለችኝ አባት እንኳን ህይወት ካላቸው በታች ከሞቱት ደግሞ የበላይ ነው የፈለገ ብንሆ ቅንጣት ታክል አይረዳንም እናም ምን ለማለት ፈልጌ መሰላቹ እኔ የ university መግቢያ ውጤት ቢመጣልኝ እንኳን ከእናቴ ጎን ሆኜ እየሰራሁ ልማር ወስኜ ነበር እናቴ ግን አይሆንም ብላ ድርቅ አለች እና እሺ ምን ላድርግ በጣም ጨንቆኛል እናቴን ማስቸገር አልፈልግም
Sep 05, 2023በመጀመሪያ ሀሳብህን/ሀሳብሽን ሳላደንቅ አላልፍም 👌አብዛኛው ነገራችን ተመሳሳይ ነው እኔ የ2014 ተፈታኝ ነበርኩኝ (3% ተማሪ ያለፈበት ማለቴ ነው) ፈተናውን ከመውሰዴ በፊት ነበር Campus ላለመሄድ የወሰንኩት እዚሁ ቀርቼ ቀን እየሰራው የማታ ለመማር ማለት ነው ውጤት ሲወጣ እኔ በጥሩ ውጤት አዳማ ደረሰኝ ለዛውም 12 አመት አብሮኝ ከተማረው ጓደኛዬ ጋር አንድላይ ነበር የደረሰን ቅርብ ቢሆንም እና ብዙ ተማሪ ለመግባት የሚመኘው ጊቢ ቢሆንም ከውሳኔዬ ፍንክች አላልኩም Family በተለይ እናቴ እንድሄድ በጣም ነበር የምትፈልግ የነበረው መጀመሪያ አካባቢ መጀመሪያ አካባቢ በጣም ጫናዎች ይኖራሉ ከ ቤተሰብ ከጎረቤት ምናምን ቢሆንም ሁሉንም ተቋቁሜ ቀን ስራ ገብቼ ማታ አዲስ አበባ University የማታ Computer Science እየተማርኩ ቤተሰቤን እያገዝኩ እገኛለው እና እኔ የምመክርህ /ሽ ውስጥህ/ሽ ካመነበት ምንም ነገር ቢሆን ከፈጣሪ ጋር ይሳካል💪 ፈጣሪ ይርዳህ/ሽ🙏
Sep 06, 2023