አንዴት ናችሁ ቤተሰብ? ፍቅረኛ አለኝ ዉጪ ነዉ የሚኖረዉ 4 አመት አልፎታል ከወጣ። የተዋወቅነዉ ለእረፍት አዲስ አበባ መጥቶ ነዉ። በጣም ቋጣሪ ወንድ ነዉ። ከ5 ዴት በኋላ ወደመጣበት ሲሄድ እኔ ከእንጨት የተሰራ ሀይማኖታዊ ስጦታ ስሰጠዉ እሱ መኪና ዉስጥ ያቆየዉን ማስቲካ አዉጥቶ ሰጠኝ። በጣም ብዙ ዉድ ነገሮች አብረን ለሌሎች ስንሰጥ ስለነበረ እኔን በደንብ ስላላወቀኝ ነዉ ብዬ አለፍኩት። 7 ወር አብረን ቆየን እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ሚስቴ ምናምን ይላል።2016 ላይ እንጋባለን ይለኛል። እኔ በብር ችግር ምክንያት ትምህርት አቆምኩ። ላግዝሽ እንኳን ስላላለኝ ከልቤ አስጠልቶኛል። ከእንደዚህ አይነት ቋጣሪ ጋር አግብቶ ቢወስደኝ እንኳን እንዴት ይኖራል? እኔ ግንኙነት ማድረግ የምፈልገዉ ከማገባዉ ሰዉ ጋር ነዉ። እሱ ቀድመን ሌላ ሀገር ላይ እንገናኝ ይለኛል። መጀመሪያ እወደዉ ነበር ወራቶች እየጨመሩ ሲሄዱ አብድለታለሁ ላልኩት ሰዉ ስሜት የለኝም። ሁሌ ይቅርብኝ የራሴን ህይወት ልኑር ስለዉ ምላሳም ነገር ስለሆነ ዉስጤ ሳያምን መልሼ እታረቀዋለሁ። በአዲስ አመት አዲስ ህይወት እንዲኖረኝ እሱን እንዴት ከህይወቴ ላስወጣዉ? ቋጣሪነቱን መጥላቴ ስህተት ሰርቻለሁ? ምከሩኝ በናታችሁ። ወንዶች ያፈቀራችኋት ሴት ተቸግራ መቋጠር ያስችላችኋል? አንዳንዴ ይህ ባህሪዉ ነዉ አያፈቅረኝም የሚያስብለኝ። ስህተት ነዉ ሀሳቤ?
Sep 02, 2023anchi techegresh esu kekuatere mnun bal ena mist honachu
Sep 02, 2023