እግዚአብሔር ፃድቅ (sooo pure & perfect) ነው እና እንደዛውም ልክ ፍፁም ፈራጅ (የማያዳላ, ለየትኛውም ኃጢያት ሳይቀጣን የማይተው) አምላክ ነው.
የኃጢያት ቅጣት ደግሞ ሞት ነው. (ሮሜ 6:23). የትኛውንም ያህል "ትንሽ ሀጥያት" ብንል ቅጣታችን የዘላለም ሞት ነው.
ለምሳሌ hypothetically ፍፁም ሀጥያት የሌለብህ ሰው ነህ እንበልና "ሰዓት ስንት ነው?" ተብለህ ብትጠየቅ, 5:01 ቢሆንና አንተ ግን "5 ሰዓት sharp ነው" ብትል ይህ በእግዚአብሔር ፊት ውሸት ነው. ለዚህ ውሸትህ የሚሰጥህ ፍርድ ደግሞ ሞት (ሲኦል) ነው. ሕይወት ለማግኘት ፍፁም ፃድቅ (perfect) መሆን አለብን.
እና የዘላለም ሕይወት አናገኝም ማለት ነው because ማንም ፍፁም ፃድቅ መሆን አይችልም??🙆♂🙆♂🙆♂ Well, the GOOD NEWS is ኢየሱስ መጣልን.
See የኢየሱስ የመስቀሉ ሥራ (ሞቱ) የእግዚአብሔር ፍፁም ፃድቅ መሆኑ እና ፍፁም አፍቃሪ መሆኑ የሚገናኙበት point ነው. ፍፁም የሆነው አምላክ ስጋ ለብሶ ቅጣታችንን (ሞት) ተቀጣልን. የኢየሱስ የፈሰሰው ደሙ በጣም pure ስለሆነ ለዘላለም የሁሉንም ሰው ኃጢያት ነው የተሸከመው (the past, the present and the future sins of every believer).
የእግዚአብሔር ፍቅሩ ደግሞ የዘላለምን ሕይወት በኢየሱስ ስላመንን ብቻ በነፃ (ፀጋ) ሰጠን. ከኃጢያት ስለራቅን ወይ ደሞ መልካም ሥራ ስለሰራን ሳይሆን በእምነት እንዲሁ በነፃ ሰጠን. (ኤፌ 2:8-9). ምክንያቱም እንደነገርኩህ በስራችን ቢሆን አንድ "ትንሽዬ" ኃጢያት ከሰራን እንኳን ሞት ነው ክፍያው. ግን እግዚአብሔር በነፃ ሰጠኝ . ይሄንን የክርስቶስን የመስቀል ላይ ስለእኔ መሞቱን በማመኔ እግዚአብሔር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘላለም ሕይወትን ሰጠኝ.
እና ከማመኔ የተነሳ የዘላለም ሕይወትን እንዳገኘው መያዣ (guarantee) የሚሆነውን መንፈሱን እግዚአብሔር በልቤ አኖረ. መንፈሱ ደግሞ በእኔ ውስጥ ሆኖ መልካም ፍሬ (ስራ) እንዳፈራ ከኃጢያት እንድርቅ እያደረገ ያኖረኛል.
እና የጠቀስከው verse ላይ እንደሚናገረው ሰው ነኝ እና ድንገት occasionally ኃጢያት መስራቴ አይቀርም ግን በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ሞትን ሳይሆን የሚፈርድብኝ በቀኙ ያለውን የልጁን ደም, የተቀጣውን ሞት አይቶ ይቅር ይለኛል. ለዚህ ነው ኢየሱስ እንዳልጠፋ ለዘላለም ጠበቃዬ የሆነው. በደሙ ምክንያት የዘላለም ሕይወትን አግኝቻለው. ለዚህ ነው አሁን ብሞት ሰማይ እንደምገባ 100% እርግጠኛ የሆንኩት.
ክብር ለሞተለኝ፤ አሁን በህይወት ኖሮ ህይወትን ለሰጠኝ፤ ለጠበቃዬ እና ለአምላኬ ለኢየሱስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን!❤️❤️❤️❤️❤️
Sep 02, 2023