ወገን እኔ ጥያቄ ጠይቄ አላውቅም ግራ ገብቶኝ ነው እስኪ መልሱልኝ🤗 አንድ ልጅ አለች እና ምንም መረዳት አልቻልኩም ሳዋራት ጥግ ድረስ ነው የምታዋራኝ እላፊ ታወራለች even ከgf ጋ የሌለኝ ነፃነት እሷ ጋ አለ በቃ እንደፈለኩ አወራታለሁ ግን ዝም ካልኩ እሷም ዝም ነው ብትሞት ወደኔ አትመጣም አንዴ ተሳስቼ ሳላያት ካለፍኩ አመት ችላ ትላለች ኮሽ አይልባትም እኔ ስሄድ ግን ፊቷ አይለወጥም እንደበፊቱ ናት እኔ luv ምናምን አልያዘኝም ግን typeኤ የምላት ሴት ናት gf ሁኚ እንዳልላት እሷ እንደዚ ባታስብስ በዚሁ እንዳልቀጥል ከኔ እስኪመጣ እየጠበቀች እንዳልጎዳት ፈራሁ ከዚ ተነስታችሁ ሀሳቧን እስኪ ገመት ገመት አድርጉ ነብሴ ተጨነቀች እኮ😭
Sep 01, 2023"...even ከgf ጋ የሌለኝን ነፃነት እሷ ጋ አለ..." & " ግን typeኤ የምላት ሴት ናት gf ሁኚ እንዳልላት..." ሁለቱ ትንሽ ክላሽ አያረጉብህም?👀 እና ደሞ በምድር ላይ ያንተ type የሚሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሲቶች አሉ እና ሁሉንም የመጠየቅ እቅድ አለህ ማለት ነው?... ምክር: አርፈህ ጥግ ድረስ እያወራህ ቀጥል። ለgfህም ጥግ ድረስ የሚያዋራትን ይላክላት!🙏
Sep 02, 2023