ይቺህ ጥያቄ #ለኦርቶዶክሳውያን አድርሱልኝ ብዙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች አሉኝ ግን አንዳቸውም መዝሙር ስያደምጡ አይቼ አለቅም። ሁሌም ዘፈን እና የዘፈን ወሬ ነው ሚያደምጡት ሌላው ደግሞ የእምነቱን ስብከት አይሰሙም እኔ የማግኘቸው ሁሉም አንድ አይነት ናቸው ማለት ይቻላል። እሁድ ጧት ጧት ቤተክርስቲያን ሄደው ስመጡ እራሱ ዘፈን ያደምጣሉ ግን ይህን ነገር ቤተክርስቲኗ ትደግፈለች እንዴ? እስቲ በመስረጃ አስተዲኝ ዘፈን መስመት መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው? እነርሱን ሁሌም እጠይቃለሁ ግን ምንም ምላሽ ልመልሱልኝ ስላልቸሉ ነው በቅንነት መልሱልኝ።
Aug 29, 2023የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደመሆኑ ዘፈንን የምትደግፍ አይደለችም። ችግሩ ምን መሰለኽ የሰዎች ጥሬነት ነው !! ይኽ ማለት ደግሞ ምን ማለት መሰለኽ ቀድሞ የአማኞቹ አለመብሰልና ፈቃደ ሥጋን በፈቃደ ነፍስ ለመተካት አለመፈለግ ሲሆን ሌላኛው ግን እነዚኽን ሰዎች ተመልክቶ የሀይማኖቱ ሥርዓት አስመስሎ ማውራት ነው። እንደዚኽ አይነት ሰው ደግሞ ሊያውቀው የሚገባው " ሰው በሥርዓተ ቤተክርቲያን እንደሚለካ እንጂ ቤተክርስቲያን በሰው ግብር እንደማትለካ ነው። ሌላው :- አጠያየቅኽን አልወደድኩትም
Aug 29, 2023