Sewoch ke afe west endi aynet ngr yewetabegnal demo negeryew yehone sheta alew mndnw miyak kale esti?
Aug 26, 2023የቶንሲል ጠጠር 🖲ከጥርስ እና ከምላስ ችግሮች ባሻገር፣ መጥፎ የአፍጠረን የሚፈጠርበት አንዱ ምክንያት ነው 🖲በተደጋጋሚ የ ቶንሲል ኢንፌክሽኖች ምክኒያት፣ በቶንሲል ከረጢቶች ውስጥ በግዜ ሂደት የሚፈጠር፣ የባክቴሪያ ስብስብ እና ተረፈምርት፣ ጠጣር ጥርቅምን ይፈጥራል 🖲ጥርቀሙ በግዜ ሂደት ይጠጥርና መጥፎ ሽታን ይይዛል። 🖲አብዛኛውን ግዜ መጠፎ የአፍ ጠረን ከመፍጠር ውጪ ፣የህመም ስሜት አይኖረውም 🖲አንዳንዴ ፣መጠኑ ከፍ ያለ ከሆነ፣ ምግብ ወይም ፈሳሽ ሲወሰድ ጉሮሮ አካባቢ በመጠኑ የመቆርቆር ስሜትን ሊፈጥር ይችላል፣ 🖲ሌላው ደሞ አንዳንዴ ከመተለቁ የተነሳ የቶንሲል እብጠት እና የጆሮ ህመም ሊፈጥር ይችላል 🖲ከዛ ውጪ የህመም ስሜት ስለማይፈጥር አብዛኛውን ግዜ በአጋጣሚ ለሌላ ህክምና በሚደረጉ ምርመራዎች ይገኛል። 🖲መጥፎ የአፍ ጠረን ካላስቸገረ እና ህመም ካልፈጠረ በቀር ህክምና አያስፈልገውም 🖲 በቤት ውስጥ የሚደረጉ ተግባሮች 👉ለብ ባለ ግማሽ ሊትር ውሀ ውስጥ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው አሟምቶ፣ ጉሮሮን በተደጋጋሚ ማለቅለቅ፣ ወይም ጋርግል ማረግ 👉 ወይም ለመጉመጥመጫ ታስቦ የተዘጋጀ የአፍ ማጠቢያንም መጠቀም ይቻላል። 👉የሚታይ ከሆነ ደሞ ግፊት ባለው ውሀ ቶንሲል ላይ በመርጨት፣ በእጅ ወይም በማይቧጭር እና ስለት በሌለው መሳሪያ ማውጣት ይቻላል 🖲እነዚህ መንገዶች ውጤታማ ካልሆኑ፣ በህክምና የቶንሲሎችን ከረጢት ማፅዳት እና እንዲሁም ከዛ ካለፈ ደሞ፣ ቶንሲልን በቀዶ ህክምና የማስወገድ አማራጭ ህክምና አለው። 🖲ይህ ህክምና የሚሰጠው በ አንገት በላይ ሀኪሞች ወይም (ENT surgeon ) ነው። አመሰግናለሁ
Aug 27, 2023