ሰላም መጀመርያ ከቤት ስትወጡ /ስትከራዩ ምን ምን ነበር የገዛችሁት /ያዘጋጃችሁት። ምን ምን ያስፈልገኛል ? ከልብ አመሰግናለሁ ለመልሱ።
Aug 23, 2023አንሶላ ብርድ ልብስ ትራስና ፍራሽ ቀስ እያልክ አልጋ ትገዛለህ፣ ከፍ ያለ ሻንጣ እሱም ቁምሳጥን እስክትገዛ፣ ስቶቭ፣ 2 ብረት ድስት አንድ የሻይ ማፍያ፣ አነስተኛ ጠረጴዛ፣ መክተፊያ ቢላዋ ሹካ ማንኪያ ጭልፋና የመሳሰሉት፣ የውሃና የሻይ ብርጭቆዎች፣ መመገቢያ ሰሃኖች፣ ባልዲና ጆግ ና ሳፋ፣ ዱካ፣ መጋረጃ፣ ላስቲክ ወለል እና ከፍራሽ ስር የምታነጥፈው ምንጣፍ፣ ከቻልክ ጫማ መደርደሪያ፣ መጥረጊያና መወልወያ ከዛ ስትኖርበት የጎደለው እየታየህ ይሄዳል። ይህ እንግዲ ለጀማሪ ላጤ ኑሮ ነው ከሰው ጋር ከሆነ ግን ብዙ ነው።
Aug 24, 2023