አብዛኞቹ ወንዶች የሰውነት ቅርጿ ያማረን ሴት በተለምዶ ( ቂጧ ወገቧ ጡቷ ) የሚባሉ አይነት ሴቶችን ሲያደንቁ አልያም ሲመርጡ እንደዚኽ ያሉ ነገሮችን ለምርጫቸው መስፈርት ሊያደርጉት እንደማይገባ ይገለፃል። ምርጫቸውን አልያም የዓይናቸው እይታንም ከእነዚኽ ነገሮች ላይ በማንሳት ልቧን አስተሳሰቧን ወስጣዊ ማንነቷን እንዲመለከት ወንዶችም ሴቶችም ስትመክሩ አያለው። ጥሩ ነው።በአንጻሩ አብዛኞቹ ሴቶች አጭር ወንድ እንደማይፈልጉ ይገልጻሉ። ዝርዝሩን ልተወውና ከዚኽ በተጨማሪ የሴቷ ቤተሰቦች እንኳ ለልጃቸው የብረት መዝጊያ የሆነ ባል ! ሲሉ ይደመጣል። (ጉድ እኮ ነው 😁) እንደው መዝጊያነቱን ትተን ደግሞ ወንዱ ሽማግሌን ሲልክ በሽምግልናው ወቅት "ምን አለው ? (እናትና አባቷ ራሱ እኮ ምንም ላይኖራቸው ይችላል ) የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የሚከበረው ገንዘብ ያለው ከሆነ በሥጋዊ ትምህርት ከፍ ያለ ደረጃን ካለው እነዚኽ ሁሉ ከሌሉት በስተመጨረሻም ቁመናው ያማረ ከሆነ ተቀባይነትን ያገኛል !! አለዚያ ሴት ልጃቸው ከልቧ የምታፈቅረው ካልሆነ ሽሙጡን አጠይቁኝ ( ያ ጉችማ ባሏ ፤ ያ ጉቶ ፤ ያ የምድር ጉድ ፤ ኤዲያ ምን ቀርቶ ለቤተሰቧ እንተውላቸው። ጥያቄ. 1. ማነው ሥጋዊ ? ጡቷ ቂጧ የሚለው ወንድ ወይስ ቁመቱ ሰውነቱ ሀብቱ የምትለው ሴት ? ወይንስ እንዲህ ያለውን ወንድ የሚመርጡላት ቤተሰቦቿ ?
Aug 23, 2023Lela werre ayasfelgewm u are absolutely achr😁
Aug 23, 2023