Hey everyone I need your advice My friend be lijinetu siweled and aynu cefuga tamo one eye blind nwe ye childhood gwadegawe negn befit lij silehone bizum bota ayestewem but now specially after 8 grade he feel low confident he is brilliant ahun first year temari nwe Le aynu teblo meneser tegeztolet neber andande Yale meneser seweta betam shame yehonal yeferal so I am trying my best so tell me what to do freinds😔
Aug 21, 2023እንደ አንተ አይነት ጓደኞች ያብዛልን ፈጣሪ ቡዙ ጊዜ አንብቤ ነው ማልፈው አልሳተፍም ይህን አይቼ አልፍ ዘንድ ህሊናዬ አላቻለም በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔር በስራው ትክክል እና አዋቂ እንደሆነ ብትነግረው እናም አውቆ ፈልጎ ባለመጣው ነገር ላይ መጨነቅ እንደሌለበትና ስለራሱ ያለውን አመለካከት በሰዎች ፊድባክ ውስጥ እንዳያደርግ እና ሁሌም ቢሆን ዛሬም ድረስ ሁለት አይናቸው ኖሮ በህይወታቸው እንብዛም ያልተደሰቱ እንዳሉ፣ሁለቱንም አይናቸው ጠፍቶ ምን አለ በአንዱ እንኳን ማየት ችዬ ቢሆን የሚሉ እንዳሉ፣ እጅም እግርም አጥተው ተመስገን እያሉ በአምላካቸው ሀሴት የሚያደርጉ እንዳሉ ብትነግረው ጥሩ ነው። ቡዙውን እኛ ሰዎች ያለንን እና የተሰጠን ላይ ከማተኮር ይልቅ የሌለን ላይ እንጨነቃለን ክፉዎች ደግሞ የሌለንን አጉልተው አሳይተው ቁልቁል ሊያወርዱን ይሞክራሉ በመጀመሪያ ማመን አለብን ካጣነው ይልቅ ያለን እጅግ ይበልጣል ስንቱ አካሉ ሳይጎድል ግን ህይወቱ የባከነ ደስታ የራቀው አለ በህይወት መኖር አንገሽግሾት ሞተለን የሚመኝ አለ በተቃራኒው ደግሞ ምንም ሳይኖረው አካሉም ጎድሎ ሀፐመ በሀፒ ሆኖ አመስግኖ ህይወት እያጓጓችው የሚኖር አለ። ሁሉም የሚወሰነው በራሳችን ምልከታ ነው እኔ የውስጤን ሰላም የምሰጠው ኮንፊደስ የሚሰማኝ ሰዎች ስለኔ ባላቸው አድናቆት እና እይታ ውስጥ ሳይሆን አምላኬ ላይ ባለኝ ግንዛቤ ነው ምንም ልሁን ግን በእርሱ አምሳል ድንቅ ሆኜ ተፈጥሪያለው ምድር ላይ እኔ ፈልጌው አለማከናወን የማልችለው ምንም ነገር የለም ሰው ነኝ መቼም 100% ፐርፌክት መሆን አልችልም ድክመት ይኖርብኛል ሰዎች ደካማውን ማንነቴ ላይ ማልለውጠው እኔነቴ ላይ አድቫንቴጅ እንዲወስዱ አላደርግም ይልቅ አክኖሌጅ አደርገዋለሁ በዛም ምንም የበታችነት እንደማይሰማኝ አረጋግጥላቸዋለሁ። እና ብሮ ወዳጅሽ በጣም ጎበዝ ነዋ ብዙዎች እርዳታውን ይሻሉ እንደሱ ቀለሜ በሆነነ ብለው ይመኛሉ እዛ ላይ አብልጦ ይሰራ ዘንድ ንገረው መለወጥ የሌለበት ነገር ላይ ጭንቀቱን ከ0% በታች ያድርግ አክኖሌጅ ያድርገው በዛ ኮንፊደንሶች እመነኝ ቡዙዎች ይኮሩበታል ደግሞ እጅ የሌላትን የፕሌን አብራሪ መኖሯን Jessica Cox እጅግ ድንቅ የሆነው Nicholas Vujicic ይመልከት
Aug 22, 2023