ምን ትሉኛላችሁ እስኪ አማክሩኝ ሰላም እንዴት ናችሁ ስሜ ዲያቆን ኢዮሐስ እባላለሁ በጣም የምወዳት የማፈቅራት ፍቅረኛ ነበረችኝ የዛሬ ሁለት አመት ነው የተገናኘው የፍቅር ጥያቄ አቅርቤላት እሺ ብላኝ አብረን ሆንን። ከዛ እሷ 12 ተፈትና ውጤት መቶላት ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ገባች እዛም እያለች ቀጠልን ነገር ግን ከእለታት 1 ቀን ባልጠበኩት ሁኔታ አልተጣላንም ግን ከዚህ በላይ አብረን መቀጠል አንችልም አለችኝ ለምን ስላት እስካሁን እወድሃለሁ አፈቅርሃለሁ ህይወቴ ሁሉም ነገር ውሸቴን ነው አለችኝ ። አትቀልጂ ብላት ቁም ነገር ነዉ አለች ። ክው አልኩ አለቀስኩ አይደለም ለዘላለም ለአንድም ቀን ሳላያት ወይም ሳንደዋወል መዋል አልችልም ለመንኳት እሺ ምክንያትሽ ምንድነው ምን አጎደልኩብሽ ምን አጠፋሁ አልኳት ምንም እሺ ምክንያትሽ ምንድነው ስላት አሁንም ምንም የለኝም በቃ እርሳኝ ካሁን በኃላ አልደውልም እንዳትደውል አለችኝ በመጀመርያ ዱርዬ ነገር ነበረች ሰንበት ትምህርት ቤት ግቢ ብያት እሺ ብላ ቤተሰብ አሳምና ገባች ዘማሪ ሆነች ለምን ንስሀ ገብተሽ ቅዱስ ቁርባን አትቀበይም አልኳት እሺ ብላኝ ቤተሰብ ግን አይሆንም አሉዋት ብቻ አሁን ከተለያየን አንድ ሳምንት ሞልቶናል ግን እኔ ልረሳት አልቻልኩም አሁንም ፎቶዋን እያየሁ ማልቀስ ነዉ ስራዬ ምን ይሻለኛ እንዴት ልረሳት እችላለሁ እስኪ ምን ትመክሩኛላችሁ 🙏🙏🙏
Aug 19, 2023ከ አንድ አመት ብሃላ ተፀፅቻለው ብላ ትመጣለች እመነኝ አሁን ግን እርሳት ብቻ ምንም እንዳልበደልካት እርግጠኛ ሁን
Aug 20, 2023