ሰላም ስሜ ብሌን ይባላል ኦርቶዶክስ ነበርኩ እና 8አመት አካባቢ ጴንጤ ሆንኩ ድሮ የነበሩ ጴንጤዎች እኔን ጌታን ተቀበይ ያሉኝ ቸርች ውስጥ ፍቅር ነበር እውነተኛ አገልግሎት አሁን ግን 4 ቸርች ሄጃለሁ ሁሉም ስለ ቢስነስ ነው ሚያወራው ጭራሽ አንዱ ፓስተር በየ ሳምንቱ ብር ብቻ በቃ አሁን ምንድነው ማደርገው የድሮ ጴንጤ የት ሄዱ አሁን ከኦርቶዶክስ የወጣሁበት ቀን ሁሌም ይጸጽተኛል ምን ይሻለኛል እንደኔ የሆናችሁ አማክሩኝ የተሰማችሁ
Aug 18, 2023ጴንጤን or ኦርቶዶክስን or ካቶሊክን መከተል እውነተኛ ሰላም እና የዘላለም ሕይወትን አይሰጥህም. መከተል ያለብህ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው. እሱን መምሰል ነው የአንተ goal መሆን ያለበት. እንደ ኢየሱስ ጠላቶችህን መውደድ, ከኃጢያት መራቅ, ሰውን እንደራስህ መውደድ,.... እነዚህ ናቸው የህይወትህ አላማ መሆን ያለባቸው. እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሕይወት መኖር ነው የሕይወትህ goal መሆን ያለበት not religion. After all it's your relationship with Jesus that matters, not religion.
Aug 19, 2023