ሰላም... እኔ አሁን ያለሁበት ቦታ ምንም አይነት ስራ የለውም እና ደሞ ከተመረቅሁ አሁን ድፍን 4 አመት ሞላኝ። ሁሉም ከኔ ጋራ ይማሩ የነበሩ ጓደኞቼ ሁሉንም ሌላ ቦታ ስራ አግኝተው ተቀጥረዋል። ብቻዬን ቀረሁ😭😭🥺 ያ ሁሉ የወጣትነት እድሜዬን በ ትምህርት ብቻ አሳልፌው(አንድ ሞያ እንኳን ሳይኖረኝ)😢 አዲስ አበባ መጥቼ መስራት እፈልጋለሁ ግን እስከዛው ለትንሽ ግዜ ስራ እስከማገኝ ድረስ እንደሌሎቹ የሚያስጠጋኝ ዘመድ ወይ ቤተሰብ የለኝም።ቤት ተከራይቼ ስራ ለመፈለግም ምንም ገንዘብ የለኝም እና አሁን ደሞ ኑሮ ውድነቱ ከአቅም በላይ ሆኗል። Addis ababa በጣም ብዙ የስራ ማስታወቂያ ስለሚወጣ እዛ ሄጄ መስራት እፈልጋለሁ ግን ከላይ እንደገለፅኩት የ የትራንስፖርት እንኳን የለኝም እና አሁን ከባድ ጭንቀት ላይ ነኝ። ብድርም ቢሆን የሚያበድረኝ የለም፤ከ መንግስት የብድር አገልግሎት ሰጪዎችም እንዳልጠይቅ ደግሞ ከ እናቴ ጋር ቤት ተከራይተን ስለምንኖር ምንም ምናስይዘው አንዳች ነገር የለንም😭😭 እና ወገኖቼ ምን እንደማደርግ ጨንቆኛል እባካችሁ ሀሳባችሁን እንድታካፍሉኝ ??🙏
Aug 14, 2023ወይኔ ወንድሜ አይዞን ፈጣሪ ይርዳህ እኔ 11ኛ ክፍል ነኝ ምንም ላረግልህ አልችልም ግን እፀልይልሀለው ኖሮኝ ብሰጥህ ደስ ይለኝ ነበር
Aug 15, 2023