Is chelsea breaking Financial Fair Play rules? If not I want reason
Aug 14, 2023የቼልሲ ገንዘብ አወጣጥና ከዚህ በኋላ ብዙ ገንዘብ እናወጣለን ለሚሉ ቡድኖች ይዞት የመጣው አደጋ ቼልሲ እንዴት ነው ያለ ቅጣት ይሄንን ሁሉ ገንዘብ ሚያወጣው ሚለውን አጠር አድርጌ ላብራራችሁ በእግርኳስ የተጫዋቾች ግዢ ላይ Amortization የሚባል ነገር አለ ማለትም የአንድ ተጫዋች የግዢ ሂሳብ ለፈረመው የኮንትራት ርዝመት ተካፍሎ የሚመጣው ሂሳብ ነው የአንድ ዓመት ወጪህ ተደርጎ የሚወሰደው ለምሳሌ ሞይሰስ ካይሴዶ ለቼልሲ ሰፈርም በአጠቃላይ Add ons ተጨምሮበት ዝውውሩ £115M የሚደርስ ሲሆን በቼልሲ ቤትም የ 8+1 ዓመት ኮንትራት ፈርሟል ይህ ማለት በ Amortization ህግ መሰረት የካይሴዶ ዝውውር አጠቃላይ ሂሳብ ሚሰላው 115÷8= £14M ብቻ ይሆናል ማለት ነው ለዚህም ነው ቼልኪ በእግርኳስ ባልተለመደ መልኩ ለሚገዛቸው ተጫዋቾች ከ 7 ዓመት በላይ ኮንትራት እየሰጣቸው ያለው ካይሴዶ 👉 115÷8=14m ኤንዞ 👉105÷9= 11m ሙድሪክ 👉 63÷8.5=7m ንኩንኩ 👉 52÷6=6m . አዳዲሶቹ ባለሃብቶች ቼልሲን ከተረከቡ በኋላ ከ 800 ሚሊዮን ፖውንድ በላይ ለተጫዋቾች ግዢ ያወጡ ሲሆን ይህ ገንዘብ ለተጫዋቾቹ ኮንትራት ሲካፈል £135M ብቻ ነው የቼልሲ የወጪ መዝገብ ላይ ሚመዘገበው ቼልሲ ደሞ በዚህ የዝውውር መስኮት ብቻ በተጫዋቾች ሽያጭ ከ £260M በላይ አግኝቷል (በነገራችሁ ላይ ከተጫዋቾቹ ሽያጭ የሚገኝ ገቢ በተለይ ደግሞ ከአካዳሚ ተጫዋቾች ሽያጭ Amortize ስለማይደረግ ቀጥታ እንደ ትርፍ ነው ሚመዘገበው) ስለዚህ ላለፉት 2 ዓመታት ያወጣው ወጪ እና ገቢ ሲሰላ ቼልሲ አሁንም £90m በላይ ትርፍ አለው ማለት ነው የሜሰን ማውንት ሽያጭ ማለትም £55M ቀጥታ እንደ ትርፍ ስለሚያዝ የ ካይሴዶን የኤንዞን ሙድሪክን እና ንኩንኩን የሁለት ዓመት Amortization almost ይሸፍናል ማለት ነው ከዚህ በኋላስ ቼልሲን ጨምሮ ሌሎች ቡድኖች በዚህ Amortization ህግ መጠቀም ይችላሉ? መልሱ አይችሉም ነው ከዚህ ቀደም የተጫዋቾች የኮንትራት እርዝማኔ ላይ በአውሮፓም ይሁን እንግሊዝ ውስጥ ያልነበረ ሲሆን ቼልሲ አነ ኤንዞን እና ሙድሪክን በ 8 እና 9 ዓመት ኮንትራት ሲያስፈርማቸው የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ስጋት ስላደረበት ማንኛውም የአውሮፓ ውድድሮች ላይ የሚሳተፍ ቡድን ከ 5 ዓመት በላይ አንድን ተጫዋች ቢያስፈርም እንኳን Amortizate ማድረግ የሚችለው ለ 5 ብቻ መሆኑን ህግ አውጥቷል ስለዚል ቼልሲ ወደ አውሮፓ መድረክ ሲመለስ ከዚህ በኋላ የሚገዛቸውን ተጫዋቾች ወጪ ከ 5 ዓመት በላይ Amortize አያደርግም ማለት ነው ዘንድሮ ታዲያ የገዛቸውን ተጫዋቾች እንዴት ያደርጋል? ቼልሲ በዚህ ዓመት የአውሮፓ ውድድሮች ላይ ስለማይሳተፍ ከዚህ ቀደም በነበረው መንገድ እንግሊዝ ውስጥ Amortize የሚያደርግ ሲሆን ነገር ግን ትላንት ማታ እየወጡ ባሉ መረጃዎች የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበርም ልክ እንደ አውሮፓ እግርኳስ ማህበር ተመሳሳይ ህግ ሊያወጣ እንደሆነ እየተነገረ ነው ቶድ ቦህሊ እና አብረውት ያሉ ሰዎች ፋይናንሻል ህጉ ላይ ያሉ ድክመቶችን (loopholes) በመጠቀም የቡድን ግንባታውን already የጨረሱ ሲሆን ከዚህ በኋላ አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር ተጫዋች በተጋነነ ገንዘብ መግዛት አይጠበቅባቸውም ማለት ነው ስለዚህ ከዚህ በኋላ ልክ አሁን ቼልሲ እንዳደረገው Amortization ላይ ያለውን ክፍተት ተጠቅሜ ገንዘብ አወጣለሁ የሚል ቡድን በአዲሱ ህግ መሰረት ከ 5 ዓመት በላይ amortize ማድረግ ስለማይፈቀድለት የ Financial Fair play ህግን የመጣስ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው እንዳላወሳሰብኩት ተስፋ አደርጋለሁ ቶድ ቦህሊ👽 @ETHIO_CHELSEA @ETHIO_CHELSEA
Aug 15, 2023