የኔ ጥያቄ ለprotestant እምነት ተከታዮች ነው እኔ ምለው ቆይ ምልጃ ማለት በእናንተ ሃይማኖት ምን ማለት ነው? ለምንድንነውስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አታማልድም የምትሉት?
Aug 12, 2023እስቲ አንድ ከመፅሀፍ ቅዱስ ጠቅሶ ሳይናደድ በስርዓት ሚያስረዳ ኦርቶዶክስ ካገኘው ይገርመኛል እስቲ አንድ ሰው👀
Aug 13, 2023የኔ ጥያቄ ለprotestant እምነት ተከታዮች ነው እኔ ምለው ቆይ ምልጃ ማለት በእናንተ ሃይማኖት ምን ማለት ነው? ለምንድንነውስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አታማልድም የምትሉት?
Aug 12, 2023እስቲ አንድ ከመፅሀፍ ቅዱስ ጠቅሶ ሳይናደድ በስርዓት ሚያስረዳ ኦርቶዶክስ ካገኘው ይገርመኛል እስቲ አንድ ሰው👀
Aug 13, 2023Will you believe me if I come up with a good argument?
Aug 13, 2023ቆይ ማርያም የት አውቃኝ ነው ምትማልድልኝ?! እንደማንኛውም ሰው ጌታን አገልግላ ሞታለች አሁን እኮ ይሄኔ እንደምትመለክ ብታቅ ደንግጣ እርሱን/እየሱስን/ ብቻ አምልኩት ብላ ነው ምትነግራችሁ። ግን ሞታለች አታቃችሁም። ሰው ናት። ጭራሽ ምስል ሰርታችሁ መስገድ እኮ ሌላ ታሪክ። ደሞ እኮ አታፍሩም ቀን ሰጥታችሁ እያከበራችኋት÷እየዘመራችሁላት÷ምስል ሰርታችሁ አየሰገዳችሁላት እያመለክናት አይደለም ትላላችሁ!!!! ዘጸአት 20 ³ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። ⁴ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። 🔊አስተውሉ ቃሉን ለምን ብላችሁ ጠይቁ ቄስ በነገራሁ ብቻ አትመሩ!!!!!!
Aug 13, 2023“የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” — ሮሜ 8፥34 ☝️መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የተፃፈው ስለእኛ የሚማልደው ብቸኛው ጌታችን እየሱስ ነው። ማርያም ሰው ናት ልዩ ያረጋት ግን እየሱስ በሷ ሊወለድ አብ ስለመረጣት ብቻ ነው። በሱ እናከብራታለን። ከዚያ ውጪ ግን ምንም ከሰው የተለየች ፍጥረት እንደሆነች መፅሀፉም አይናገርም። እኛ ደግሞ ምናምነው የተፃፈውን ነው። ደግሞም ምንም ያክል ማርያም ልዩ ብትሆንም መላእክትን ጨምሮ ስግደት፣ምስጋና እና አምልኮ አንዳቸውም አይገባቸውም ወደእነርሱ አንፀልይምም አይሰሙንምም። 10ቱ ትዕዛዛት ላይ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ የሚለውን ዋናውን ህግ አትርሱ። የምትከራከሩ ሰዎች ደሞ በመፅሀፍ ቅዱስ አስረዱ አለበለዚያ አይገናኝም። ማምለክ: ማንኛውም ስግደት ልዮ አክብሮት እና መስዋዕት ከአምላክ ማስበለጥ ነው። 👉ዘጸአት 20 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። ⁴ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። ⁵ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
Aug 13, 2023ዮሐ6፡44 "አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።" ይላል ስለዚህ በእናንተ አባባል ከሆነ እዚህ ጋር ደግሞ አብ አማላጅ ነው ልትሉ ነው? ከሆነ ማነው ተማላጁ/ተለማኙ/? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረትን የሚሰጥ እንጂ የሚለምን አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ አስገኚም ሰጪም ራሱ ነውና ምሕረትና ይቅርታም የባሕርይው ስለሆነ እርሱ ራሱ የሚሰጠን ይቅር የሚለን የሚያነጻን እንጂ ከሌላው የሚቀበለው ነገር የለም። ዮሐ 5፡8 "ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።" የመጻጉን ኃጢአቱን ያስተሰረየለት ይቅር ያለውና ከደዌውም ያዳነው እርሱ ነውና።
Aug 13, 2023Asker gen ሮሜ 8:13 አንብበህዋል ቃል በቃል እየሱስ እንደሚማልድ ነው ሚያወራው። አብ እና ወልድ እና መንፈስቅዱስ ደሟ በአካል 3 በመለኮት አንድ ናቸው አታምታታ። ደግሜ ልጠይቅ ለዚህ ጥቅስ ማብራሪያ ስጡ?!!! ደግሞ ማርያም ታማልዳለች የሚል ጥቅስም አምጡ????!!! 👉“የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” — ሮሜ 8፥34
Aug 13, 2023Eyesus ayamaledem metelut lemndenew
Aug 13, 2023ምክንያቱም ምሕረትን የሚሰጥ እንጂ የሚለምን አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ አስገኚም ሰጪም ራሱ ነው ምሕረትና ይቅርታም የባሕርይው ነው እርሱ ራሱ ነው ይቅርታን የሚሰጠን። ደግሞም እርሱ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። ዮሐ 10፡30 "እኔ እና አብ አንድ ነን" ዘጻ 32:36 "...እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል ስለባሪያዎቹም ያዝናል።"
Aug 13, 2023Lady you gotta mean this, this is no game it's your life man make decision for the last time and start to love->respect yourself don't be taken for granted he is not worth it so first confess all your sins to your God and start new life with new personality, learn from you past experiences and move on after taking the lesson and work on your self to change,I know change is not easy but it's possible all the time and do you beat and let God to do the rest😊 may God help you sister 💖🙏
Aug 13, 2023Ezih gar menager mfelgew ngr mejemeriya sgdet hulet nw ye tsega ena ye amlko ye tsega segdet le tsega lalachew hula ygebal eshi le emebrhanem ygebatal enante mtlewtut aydelem yehen metsehaf kidus ly temelketu tsadkan ye alem brhan nachew yelale enante esun atkdum lela demo melja malet ante sle ene ene sle ante wede lela sew senteyk nw be metsehaf kidus demo wede egziabher memaled nw and ngr atesasatu ye egziabher ayn ena joro wede tsadkan nw yelale metsehafu ena lmndn nw matamaldew tsadk bathon esun teweldew nbr sle melja lemawrat demo kefelegachu eyob ly hedachu manbeb techelalachu ye eyob guadegnoch tefat atfetew tseleyu gn altesemalachewm kezam eyob tseleye enam egziabher sle enante bye sayhon sle eyob bye markuachu ale melja yehe nw eshi siketl fetari bemiyargbet gize wede abatum be kegn likemet arege meljan hulu le tsadkan sete yelale pls anbebu manm ye mamaled seltan baynorew noro enante church wst tseleykulh yehonlehal tfewesaleh enen kante yebelete geta ysemagnal baltebabalachu nbr rasachu metadergut ngr kemtamnut ngr gar clash yadergal rasachehun zor belachu temelketu
Aug 16, 2023ተጨማሪ ከፈለክ you can DM, put your username.
Aug 14, 2023Neriah: የቃላት ፍቺ 1) “ማለደ” ማለት “ለመነ” “ደጅ ጠና” ማለት ነው፥ 2) “አማላጅ” ማለት “በለማኙ ስም ተለማኙን የሚጠይቅ እና የሚለምን ሦስተኛ ወገን” ማለት ነው። ክፍል አንድ #የቃላት_ትርጋሜ በቅድሚያ #ማለደ #አማለደ #አማላጅ #ማላጅ ተማላጅ(የሚማለድ) #ምልጃ #ጠበቃ እና አስታራቅ የሚሉትን የቃሉን ትርጉም እንመለከት፡፡ #ማለደ 1፡-የሚለው ቃል ሁለት ዓይነት ትርጉም ሲኖረው የመጀመርያው ማለደ ማለት በማለዳ ወይም በጥዋት ተነሣ ማለት ነው፡፡ለምሳሌ‹‹መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር #ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰው ትመስላልችና፡፡››ማቴ20÷1 ‹‹ሕዝቡም ሁሉ ይሰሙት ዘንድ #ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር››በሉቃ 21÷38 ‹‹አቢሜሌክም በነጋታው #ማለደ ባርያዎቹን ሁሉ ጠራ››ዘፍ20÷8 ‹‹ሳሙኤልም በነጋው ሳኦልን ለመገናኘት #ማለደ››1ሳሙ 15÷12 ‹‹ቃልህን አስብ ዘንድ ዓይኖቼ #ለመማለድ ቀደሙ›› መዝ119÷148 ማልዶ፡ማልደው፡ማለደ ና ለመማለድ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱ ሳይነጋ መነሳት ማለት ነው እንጂ በጸሎት ፈጣሪውን #መለመን ለማመለከት አይደለም፡፡ #ማለደ ለሚለው ቃል ሁለተኛው ትርጉም ለመነ፡ደጅጠና የሚል ትርጉም አለው፡፡ለምሳሌ፦ በሥጋ ወራት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ደቀመዛሙርቱ ማልዶአል(ለምኖአል)ሉቃ 22÷32፤የእስራኤል ሕዝብ ለእግዝአብሔር አልታዘዝም ስሉ ለእርሱ አልታዘዝ ያሎትን አጥፍቶ አድስ ትውልድ ለሙሴ ለመስጠት ስያስብ ሙሴ እግዝአብሔር ሕዝቡን እንዳያጠፋ ማልዶአል፡፡ዘኀ14÷19፤አብርሃም ለሰዶም #ማልዶአል ዘፍ18÷16-33 #አማለደ፡-የሚለው ቃል በግእዝ ግስ‹‹ተነበለ››ማለት ሲሆን ይህም በሁለትና ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች ወይም ወገኖች መካከል የተፈጠረውን ቅራነ እና ጠብ እንድወገድ አደረገ አልያም አስታረቀ ማለት ነው፡፡የሚለምነው ሰው ለማኙን ይቅርታ እንድያደርግለት ና በመካከላቸው ሰላም እንድወርድ በለማኙ ስም ተማጸነ ማለትነው ፡፡ #አማላጅ፡-ማለት አንድ ሰው በራሱ ማድረግ የማይችለውን ለምኖ የሚያስደርግ አማላጅ ይባላል፡፡አንዱ ለሌላው ይቅርታን እርቅን ሰላምን ለማስገኘት በአድራጊውና በተቀባይ መካከል የሚያገናኝ #መስመር ነው ፡፡ ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ አማላጅ ነበር እንዲሁም ሊቀካህናትም አማላጅነበሩ፡፡ ክፍል ሁለት #ማላጅ፡-ሁለት ሰዎች እንድግባቡና አንድ ሰው ተቀባይነት እንድያገኝ የሚለምን #ማላጅ ይባላል፡፡ #ማስታረቂ[2] ፡-የሚለው ቃል”katallasso”ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ምንጩም kata/ካታ እና allosso/አሎሶ ከሚል ሁለት ቃላት የተገኘ ነው፤ትርጉሙ በሁለት ወገኖች መካከል ወዳጅነትን ማስፈጠርና ማስማማት የሚል ትርጉም አለው፡፡ #ምልጃ[3]፡-ማለት የመለመን አገልግሎት ማለት ነው፡፡ምልጃ መለመን ብቻ ሳይሆን የማስታረቅም አገለግሎት ነው ፡፡ማስታረቅና መለመን የቃል ፍቻቸው ቢለያይም አላማቸው ግን ተመሳሳይ ነው ፤ይህም የራቁ እንድቀርቡና የተጣሉ እንድታረቁ የሚያደርግ አገልግሎት ነው፡፡ኤፈ1÷16፤6÷19 መጸሐፍ ቅዱስ ለሌሎች እንድንማልድ (እንድንጸልይ) ያዘናል፡፡ስለ ሌሎች መጸለይ ወይም መማለድ ለክርስትያኖች ሁሉ የተሰጠው ሃላፍነትና አገለግሎት ጭምር ነው:፡በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለሌሎች የማለዱ ሰዎችአብርሃም ዘፍ18÷1-33፤ዳዊት መዝ72÷1-20፤ የኢየሱስ እናት ማርያም ሉቃ1÷46፥55፤ ሐዋርያዊ ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 10÷14፤ ጢሞቴዎስ ጢሞ 2÷1-7…ወዘተ ናቸው በምድር ላይ ሌላ ለሌላ መስበክም ማስተማርም መጸለይ ሆነ መምከር ይችላል፤ግን ይህ መስበክ ማስተማር መጸለይ ሆነ መምከር ገደብ አለው ገደቡም ይህም በአጸደ ሥጋ ማለትም በምድር ላይ እያሉ ብቻ ነው፡፡ከሞት በኃላ መጸለይ ሆነ መስበክ የለም ይልቁንም ዕለት ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስክርስትስን ማሚለክ እንጅ፡፡በአዲስ ክዳን ክርስትያኖች ፀልዮ ተጽዕኖ ማምጣት ይችላሉ፤ነገር ግን በሰማያዊ(በትንሣኤ) አካል ሆኖ በሞቱ ሰዎች ላይ ምንም ተጽዕኖ አያመጡም፡፡ይህ ማለት በቅዱሳን ምልጃ አማካኝነት ነፍስን ከሲኦል ወደ መንግስት ሰማያት፤ከመንግስት ሰማያት ወደ ሲኦል ማስገባት ሆነ ማስወጣት ለማንም አልተሰጠም ፡፡ይህን ስልጣን ያለው #የሞትና_የሲኦል_መክፈቻ_አለኝ_ያለው_የይሁዳ_አንበሳ_የናዝረቱ_ኢየሱስ_ብቻ_ነው፡፡እንዲህ ስባል ግን ኢየሱስ ወደ ሲኦል የገቡትን ያድናቸዋል ማለት ሳይሆን በሞትና በሕይወት ላይ ስልጣን እንዳለውም ለማሳየት ያህል ነው፡፡ዕብ9÷27.
Aug 14, 2023I have a question for the protestant ppl and tsehuf esti amtu ke metsehaf kdus ly maryam atamaldm yemil esti yet ale
Aug 16, 2023