ሰላም ሰዎች እንዴት ናችሁ? በተለይ ኦርቶዶክስ የሆናችሁ እንድትረዱኝ እፈልጋለው።እኔም ስለሆንኩ ማለት ነው። ውስጤ በከፍተኛ ድብርት እየተጠቃ ነው።ድብርቱም በሌላ ሳቢያ እንዳይመስላችሁ ወደሀይማኖቴ ለመቅረብ ባደረግኳቸው የተወሰኑ ሙከራዎች ሀይማኖቴን ሊያስክድ የሚደርስ ትልቅ ጨለማ ውሥጤ ላይ ይነሳል።የማያባራ ጥያቄ ውስጤ ይጠይቃል።እኔ ኃጢአተኛ ነኝ።ንስሐ ብቻ ነው ማሰብ ያለብኝ ብዬ ንስሐ ልገባ ስል አሁንም መዓት የሀይማኖት ጥያቄዎች ውስጤ እየመጡ እና በቃ አለ አይደል አንዳንዴ ሀይማኖት የሰዎች ፈጠራ እስኪመስለኝ ትርጉም አልባ ያደርግብኛል።አሁንም በትልቅ ጭንቀት ውስጥ ነኝ።በአንድ በኩል ደግሞ ፈጣሪ የሚቀስፈኝም ይመስለኛል። መፍትሔ ካለኝ ንገሩኝ።የልጅነት ልቤን ማግኘት አልቻልኩም።
Aug 10, 2023Maybe that's a good thing. ትክክለኛው "የኦርቶዶክስ ሃይማኖት or ፕሮቴስታንት" ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ነው. መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳህ ፀልየህ መፅሐፍ ቅዱስን አንብብ. እውነት ክርስቶስ እንጂ "ሃይማኖት" አይደለም. ሃይማኖቴ እውነት ነው ካልክ ከኢየሱስ የሚበልጥ እውነት አለ ነው የምትለው, መቼስ ኦርቶዶክስ ኢየሱስ ነው አትልም. So brother ድርሳናት ምናምን የሚባሉ ተረት ተረቶችን ትተህ ኢየሱስን ፈልገው እሱም ቃል ነው.
Aug 10, 2023