እኔ እግዚአብሔር ለአንተ እድሜ እንዲሰጥኽ እመኛለው ! ጃውሳም በለው ፋኖም በለው ነፍጠኛም በለው ብቻ ምንም በለው ነገር ግን ይኽ ጊዜ እንዳይመጣ በአበው ዓይን ተረድተንና ተመልክተን ያየነው ተናግረናል መስክረናል አስጠንቅቀናልም ሆኖም ጥፊ ያላት ሀገር አታሞ ቢመታ አትሰማ እንዲሉ እንቢ ብሏልና መትውልድ ቅጣት መጥቷል ! ወደድኸውም ጠላኸውም መጻኢ ድል የዐምሐራው ሕዝብ ነው ! የሚያልቀው ያልቃል ! እኛም ሟች ነን ! ይኽን ቀን ጠብቀን ነበር ዛሬ መጥቷል ውጊያው ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም። ፍፃሜው ከሁለት ወንዞች ነው ! ጫጩት ፊት ፈንግል ላይወራ ከእሾኽ ላይ ዘር ላይዘራ ሆነና አሁን ዝም አልን እንጂ በጠዋቱ መክረን ነበር። ከ2ዓመት በፊት ምልክት ትሆናችኹ ዘንድ ከአበውም ከቃሌም ስህተት እንደሌለ ታምኑና ንስሐ ትገቡ ዘንድ በዚሁ ቻናል ላይ በተጠየቀ ጥያቄ ላይ አሜሪካ በወር ውስጥ የሚገጥማትን በጥቂት ገልጬ ነበር በወሩ ሲከሰት ዳግም የመለስኩት ምላሽም ነበር። በጊዜው አድምጣችኹ በንስሐ የተመለሳችኹ እንዳላችኹ ጽፋችኹልኝ ነበር። ቀን ቢረዝም ልብ ይደክም ነውና ቀኑ ቢረዝም ሀሰት እንዳልሆነ ተረድታችኹ አሁንም በንስሐ እግዚአብሔርን በመለመን እንድትፀኑ አሳስባለው። ቀኖች ክፉዎች ናቸውና !! ወንድሜ Ito አንትም ብትሆን ከልብኽ ያለውን መለስ ብለኽ መርምርና ከቻልክ ከእውነት ለመድረስ ካልቻልክ ግን ዝም ለማለት ጣር አለዚያ ምሕረት ለአንተም ለዘርኽም አይኖርም ! ! በመጨረሻ እኛ እያለቀስን እንስቃለን !! ድላቸውንም እንጠብቃለም። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማች ከፍ ብላ ልትውለበለብ ተዋህዶአችን የማንም ክፍት አፍ - አፍመክፈቻ ከመሆን ተላቃ ልትታፈር ቀናት ቀርተዋልና ፋኖዬም ነፍጠኛዬም ጃውሳዬም ኢትዮጵያዊ ትግሬዬም ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዬም ደብብዬም አፋርዬም ወደፊት !!! ሲነገርሽ እንቢ ብለሽ ዛሬ ላይ መጨነቅሽ ምን ሊፈይድሽ እሰይ መዓት መጣልሽ ምን ይውጥሽ የት አባሽ !! 💚💛❤️
Aug 10, 2023