Question for Muslims, -Do you feel unheard in Ethiopia? -Do you think Ethiopia is dominated by Christian and its ideology? -Whats your plan for the future as a people? It might be a sensitive question so leave your emotional on the door before answering...
Aug 08, 2023- ከአጤ ሐይለ ሥላሴ በኋላ እንዲህ አይነት ጭቆና ስለቀረ 'አልተደመጥንም' ብዬ አላስብም። አባባሌን ሁሉም ቢረዳው መልካም ነው። ሁሉም ነገር ተሟልቶልናል ማለት ሳይሆን ከአጼዎቹ ዘመን የጠመመ አስተዳደር በእጅጉ የሚሻልና እኩል ለመሆን የቀረበ ነው። ለምሳሌ አሁን ክርስትና አንዴ በኦሮሚያ ሌላ ጊዜ በትግራይ እየተከፋፈለ እያየን ነው። ይህ ማለት ክርስትና አበቃለት ማለት አይደለም። በተለያዩ ዘመናት የተለያዩ ሁኔታዎች ሙስሊሙ እንዲጨቆን አድርገውታል። ያ ደግሞ በሐይማኖቶች ላይ የሚስተዋል ነው። በመለስ ዘመን ትንሽ ጠማማ ስራ ቢሰራ አላህ ቀሰፈው። ተያ ውጭ ዴየግ ነን። - ድሮ ድሮ 'ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች' ከሚለው የክርስቲያኖች ልፈፋ ተነስቶ እስከ "የአሞራ አገር ዋርካ የሙስሊም አገር በካ" የሚለው የአጼ ሐይለ ሥላሴ አገላለጽ ኢትዮጵያን የክርስቲያን ብቻ አድርጎ የመሳል አባዜ ነበር። ባይሳካላቸውም! አሁን ላይ ግን በአፍ ከመጠየቅ ይልቅ በተግባር ደረጃ ማን ኢትዮጵያን እየጠቀመ እንደሆነ ማየት ቀሏል። - እንደ ሙስሊም ለወደፊቱ ማሰብ ያለብን መጀመሪያ ራሳችንን ከርክሰት ማጽዳት ነው። አላህ ያዘዘንን መተግበር የከለከለንን መከልከል። እኔ ከዝሙት፣ ከውሸት፣ ከስርቆትና ከሌሎች ወንጀሎች ሳልጸዳ አገሪቱን የሙስሊም ማድረግ ባስብ ይህ ከንቱ ነው። ስለዚህ እንደሙስሊም ራስን ከወንጀል ማቀብ የመጀመሪያ መንገዳችን ቢሆን የትኛውንም ጀብድ ለመፈጸም ከባድ የሚሆን አይደለም። በመጨረሻም የምለው ሁሉም ራሱን እኩል እንጂ የበላይ አድርጎ አይመልከት። ከዚያ ውጭ ምርጫም የለንም። ውጤቱም ክፉ እንጂ አይሆንም። እኔ ደግሞ ላንተ ጥያቄ አለኝ.. ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ ምን አነሳሳህ? ከላይ የጠየቅካቸውን 3 ጥያቄዎች ወደራስህ አዙረህ መልስልኝ።
Aug 09, 2023