ከፍቅረኛዬ ጋር ሶስት አመት በፍቅር ቆይተናል። ግንኙነትም ፈፅመናል ነገር ግን ከወር በፊት እስከምንጋባ ግንኙነት አናደርግም ስትለኝ ተቀበልኳት ነገር ግን ተራርቀን ስለምንኖር ቢያንስ ስንገናኝ ራሳችንን ጠብቀን አብረን እንደር ስላት ከአንተ ጋር ምሽት ማሳለፍ አልፈልግም አለችኝ። ምን ላድርግ ምከሩኝ ( በድንግልናም አላገኘኋትም).
Aug 08, 20231. በድንግልና ስላላገኘሀት ከትዳር በፊት ሩካቤ ያለመፈፀም መብት የላትም ማለት አይደለም። (ማንኛውም በድንግልና ያልተገኘች ሴት ጨምሮ) 2. ግንኙነት የፈፀማችኹት ለምን ያኽል ጊዜ እንደሆነ ባላውቅም አሁን ላይ የወሰነችው ውሳኔ ግን ትክክል ነው። 3. ተራርቆ አብሮ ማደር ግልፅ አልሆነልኝም። 😂 ሩካቤ ሳትፈፅሙ ለማለት ይመስለኛል ግን ይኽም ትክክል አይደለም ! ቀን አብራችኹ ዋሉ !! 4. አብረን እናምሽን ግን እንቢ ማለቷ ለምን የሚያስብል ነው ! ለምን ? የት ነው የምታመሹት ? የምታመሹበት ስፍራ መፈፀም የለብንም ያለችኽን ተግባር እንድትፈፅሙ የሚያመች ከሆነ ትክክል ናት ካልሆነ ግን ከጀርባው አንዳች ምክንያት ይኖረዋል ! ምከሩኝ ብለሀል እንግዲ ተቀበል !! አብሮ ለማደር መጠየቅኽን አቁምና መለስ ብለኽ ግንኙነታችኹን መርምር።
Aug 08, 2023