ሰላም ለእናንተ ኦርቶዶክዊያን! ከቅዳሴ ራሴን ከራቅኩ ወደ ዓመት ይሆነኛል።በጣም ከባድ የሆነ ኃጢአት ስለሰራው ከእነዚህ ኃጢአቴ ትልቁ ስርአት ላይ መቅረብ ስለፈራው ነው።አሁን ደግሞ የእመቤታችን ፍልሰታ መጥቶአል።ንስሐም አልገባውም። እና ምን ትመክሩኛላችሁ? ንስሐ ገብቼ ቀኖና እስክጨርስ በዚሁ ልቀጥል ወይስ ምን ምንድነው ከቅዳሴ የሚያስከለክለን???
Aug 06, 2023እግዚአብሔር ኃጢአተኛን ሳይሆን ኃጢአትን ነው የሚጠላው፡፡የይሁዳ ትልቁ ኃጢአት ጌታን መሸጡ ሳይሆን ንስሐ አለመግባቱ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታል ነች ሆስፒታል ደግሞ ለበሽተኛ ነው የሚያስፈልገው ሰለዚህ ቤተ ክርስቲያን ለእኛ ኃጢአተኞች የተዘጋጅች ናት ከባድ ኃጢአት ስለሰራን የምንርቅበት ሳይሆን እንደውም መድኃኒት ለማግኘት መሄድ ነው ያለብን ምንም ኃጢአት ብንሰራ ጥቂት ጸጸት ብናሳይ ይቅር ሊለን የታመነ ነው፡፡ሰው ለመጥላት ምክንያት ይፈልጋል።እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ጥቂት ምክንያት ይፈልጋል።በአጠቃላይ ንስሐ ገባቹም አልገባቹም በፍጹም ትልቅ በረከት በሚገኝበት ፍልሰታ ቅዳሴ እንዳትቀሩ!!!እና ደግሞ በዛው በጾሙ ንስሐ ገብታቹ ቀኖና እየፈጸማቹ ማስቀደስ ትችላላቹ ግን ማስቀደስ እየቻላቹ ግዜ እያላቹ ንስሐ አልገባውም ብላቹ መቼም ቅዳሴ እንዳትቀሩ በተረፍ እግዚአብሔር ይርዳቹ።
Aug 06, 2023