#ኦርቶዶክስ እህት ወንድሞች ተባበሩኝ ፡ ይህ ጥያቄ እንድንሰራ ተሰጥቶን ነው። 1ዱንም ብተምልሱልኝ አመሰግናለሁ። 1. አንድ ሰው አንድ ህግ ቢተላለፍ ሁሉን እንዳፈረሳቸው ይቆጠራል ፡ እንዴት ? 2. ህግ የተሰራላቸው በህግ ይቀጣሉ ።ህግ ያልተሰራላቸው ደግሞ ብህገ ልቦና ይፈረድባቸዋል ሲባል ምን ለማለት እንደሆነ አብራሩ ? 3. ቅድስት ቤተክርስትያናችን ከቅድሳት ስዕላት በስተቀር በተቀረጹ ነገሮች አምልኮ እንዳይፈጸም ትከለክላለች ። ይህ እንዴት እንደሆነ አብራሩ? 4. ለበዐላት መከበር መነሻቸው ምንድን ነው? በዐላት እንዴት መከበር ይገባቸዋል? 5. ህገ ወንጌል ከህገ ኦሪት የምትለየው በምን ምክንያት እንደሆነ አብራሩ። 6. እግዚአብሄርን ማምለክ የሚገባው በ እውነት እና በመፈንስ ነው ነው ሲባል ከህግ አንጻር እንዴት እንደሆነ አስረዱ።
Aug 05, 20231) አትግደል ተብለህ ብትገድል ገደልክ እንጂ አመነዘርክ ወይም ሌላ አትባልም። ይሁዳ ሲክድ ካደ ተባለ፣ ሄሮድስ ሲገድል ገደለ ተባለ ሲጠየቁ በበደሉት በደል ነው። የኛ ሥራ ስንበድል ተጠያቂ ከመሆናችን በፊት የእግዚአብሔር ምሕረት ጠያቂ መሆን ነው። 2) እኛ ክርስቲያኖች የምንቀጣው በክህደታችን ልክ እንጂ በበደላችን በመተላለፋችን አይደለም። በሕገ ልቦና የነበሩት እራሳቸው በሠሩት ሕግ ይቀጣሉ፥ በኦሪትም ዘመን በሕገ ኦሪት ይቀጣሉ። እኛ በዘመነ ወንጌል ያለነው ደሞ በሕግ የምንቀጣ ሳይሆን በምሕረቱ በቸርነቱ የምንድን፤ እንደበደላችን ሳይሆን እንደ ይቅርባይነቱ የምንኖር ነን። 3) ቤተክርስቲያን የስዕላትንም ሆነ የምስል ቅርጽ አምልኮን አታስተምርምም አትፈጽምም። የሚመለከው ሥሉስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስዕላት እግዚአብሔርን፣ ቅዱሳን መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን የምንዘክርበት ንዋይ ነው። የምስል ቅርጽ as the matter of tradition ይከለከላል። 4) የትኛው በዓል የሚለው ጥያቄው የሚፈጥር ቢሆንም ሁሉም በዓላት እግዚአብሔርን በማመስገን፣ ቅዳሴ በማስቀደስ፣ ሥጋሁ ወደሙን በመቀበል፣ የታመሙት በመጠየቅ፣ የታሰሩትን በማጽናናት ብናደርግ መልካም ነው። 5)ሕገ ኦሪት ሕግ ብቻ ነው። ይህ ከሆነ ይህ ይሁን የሚል ትእዛዝ አለው። ሕገ ወንጌል ግን ፍቅር ነው። ውስጥ ያለው ፍቅር የተባለው ክርስቶስ ነው። እንደ ኦሪት የጠላህን ጥላ ሳይሆን ጠላትህን ውደድ ነው፣ የሚረግሙህን መርቅ ነው። 6) እቺ ነገር ሳትምታታብህ አልቀረችም። እውነት የተባለው ወልድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መንፈስ ደሞ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ነው። አብን ከወልድ፣ ወልድ ከመንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስ ቅዱስንም ከአብ ነጥለህ ማምለክ አትችልም። እግዚአብሔርን ማምለክ ራሱ ትልቅ ጸጋ ነው። ቅዱሳን ጻድቃን ዓለምን ንቀው ቁመው እግዚአብሔርን ሲያመስግኑ በራሳቸው አቅም አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስ እራሱ አነሳስቶአቸው እንጂ። በጨበጣም አይደለም፥ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ እውነት የሆነውን ወልድን እያሰቡ እንጂ። እግዚአብሔር ከሰማየ ስማያት ወርዶ በቅድስት ድንግል ማኅጸን አድሮ ተወልዶ ያዳነን ፍቅር ስቦት እንጂ ሕግ አስገድዶት አይደለም። እኛም ስናመልከው በሕግ ሳይሆን ለኛ ያለውን ፍቅር እያሰብን ነው።
Aug 10, 2023