👋hey Q for muslims Please explain what is Sufi selefi ahbash wahabi Enezi mndnachew egnas kenezi wst nen wey?
Jul 23, 2023ሰላም ወደ መልስ የምሰጥህ መልስ ጠለቅ ያለ አይደለም። ለተጨማሪ ማብራሪያ ከኔ የተሻሉ ካሉ ይመልሱልሃል። ሱፊይ: ይህ ስያሜ 'ሱፍ' ከሚለው የዓረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን መነሻው ደግሞ በሆነው ዘመን ላይ (ጊዜውን በትክክል ስለማላውቀው መጥቀስ አልችልም) የነበሩ አላህን በጣም የሚፈሩ መዘውተሪያቸው መስጂድ የሆኑ፣ ከዚህች ምድርና በውስጧ ካለው ብልጭልጭ ተብቃቅተው ፊታቸውን ወደ አላህ ያዞሩ፤ በዚህም የሚለብሱት ልብስ ከሱፍ ጨርቅ የተሰራ ሰዎች ነበሩ። በልብሳቸው የተነሳ ነው ይህን ስያሜ ያገኙት። ልብ እንድትልልኝ የምፈልገው ይህ ስያሜ የተሰጣቸው ጥያታዊያን ሱፊዮች እና ዛሬ ያሉት ጨምላቃ ሱፊይ ነን ባዮች በጣ.......ም ይለያያሉ። እነዚያ ሱፊዮች ስራቸው ወደ አላህ መቃረብ ብቻ ሲሆን የዛሬዎቹ ግን ስራቸው ሆን ብለው የሚለያየንን መንገድ በመፈለግ መለያየት ነው። በድሮዎቹ ሱፊዮች መስመር ከሆነ ሁላችንም ሱፊያዎች ብንሆን ወደ አላህ ለመቃረብ የበለጠ ነበር። ሰለፊይ: ይህ ደግሞ ትክክለኛውን የነቢዩ ሙሐመድን መንገድ የተከተለ ሰው መጠሪያ ነው። የነቢዩ ባልደረቦችም የነቢያቸውን መንገድ አጥርተው የተከተሉ ሰለፊዮች ነበሩ። አሕባሽ: በአብዱላህ አል-ሐረሪ (1960ዎቹ አካባቢ የነበረ ሰው) የተመሰረተ ፊርቃ/አንጃ ነው። ሰውየው ኢትዮጲያዊ/'ሐበሻዊ' በመሆኑ በዓረቦች የተሰጠው ስያሜ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ መንገዱን የሚከተሉ ሰዎች አሉ። ነገር ግን በጣም ጥቂት ናቸው። 'ሉብናን' ውስጥ ከየትኛውም ቦታ በላይ በስፋት ተከታይ አለው። ከሱፊዮች ጋ መመሳሰል ቢፈልጉም የሚለያያቸው ነገር አለ። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ለአንድ ነገር ሲሉ ሁለቱም ተዋህደው አሉ፤ እርሱም እነርሱ ወሃቢይ ብለው የሚጠሩትን ቡድን ማጥፋት። ለዚህ ሲሉ አብረው ይሰራሉ። (የተዋሃዱት ለአላህ ብለው ሳይሆን ሙስሊም ወገኖቻቸውን ለመውጋት በመሆኑ ኋላ ወደ እርስ በራሳቸው መዞራቸው አይቀርም። ይህ የግል ምልከታዬ ነው።) ወሃቢይ: ይህ ስም መነሻው 'ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል-ወሃብ ከተባለ ግለሰብ ነው። ይህ ስም የተሰጣቸው ሰዎች ስለዚህ ግለሰብ ሲተርኩ "ከ 200 አመት አካባቢ በፊት የነበረ ግለሰብ ሲሆን በሳዑዲ አረቢያ ምድር ላይ የአላህ ዲን በወንጀልና መጤ/ቢድዓ በተሞሉ ነገሮች ሲበከል እነዛን መጤ ድርጊቶች በሙሉ ያወገዘና ያጠፋ" እንደሆነ ይናገራሉ። ይህን ድርጊቱን የተቃወሙና መጤ ድርጊቶቹ እንዳይት-ተዉ የፈለጉት ግለሰቦች ይህን ሰውና የተከተሉትን ሁሉ ከስሙ በመውሰድ 'ወሃቢይ' ብለው ፈረጇቸው። ወሃቢዮች ራሳቸውን ወሃቢይ ብለው ባይጠሩም በማይወዷቸው ወገኖች ግን እየተጠሩበት ነው። እንድታውቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር 'ወሃብ' ከ 99 የአላህ ስሞች አንዱ ነው። እኔ ወሃቢይ(የአላህ) ብለህ ብትጠራኝ ክፋት የለውም።😇 አንዱ 'ወሃቢይ' ብለው ቢሰድቡት ምናለ መሰለህ.. "ወሃ-ጠጪ እንጂ ወሃ-ቢ ሲባል አላውቅም።" አላቸው።😄 የድሮዎቹ ሱፊዮች፣ ሰለፊዮችና ወሃቢዮች ሁሉም አንድ ናቸው። አላህ የከለከለውን ተከልክለዋል፤ የፈቀደውን ሰርተዋል። አሕባሽና ዘመናዊው ሱፊያ ግን ከ 50-60 አመት እድሜ ያለው በቢድዓ እና በሺርክ ጨምለቅለቅ ያለ አንጃ በመሆኑ ከነርሱ እንድትርቅ እመክርሃለሁ። ከነርሱ ይልቅ አምሓራ ክርስቲያኖች ይሻሉናል። እኛ ሙስሊሞች ነን። ይህ ደግሞ አላሁ ተዓላ የሰጠን ስም ነው። ሌላ መጠሪያ ሊኖረን አይገባም። ራስህን ከነዚህ ስለመመድብ ሳይሆን ማሰብ ያለብህ ቁርአንና ሐዲሡን መከተል ነው ያለብህ። የዛኔ ለጀነቱ ቅርብ ነህ። ካልሆነ ግን ነቢዩ "ኢስላም ወደ 72 ቦታ ይከፋፈላል፤ ከአንዱ በቀር ሁሉም የእሳት ናቸው። የጀነት መንገዱም የእኔ እና የባልደረቦቼ መንገድ ነው።" ብለዋል። አንተ የሆነው አንጃ ትክክል መስሎህ ተከትለህ ከጀነቱ መንገድ ብትወጣ መዳረሻህ እሳት ስለሚሆን ከዚህ እሳቤ ወጥተህ ራስህን ሙስሊም ብለህ ብቻ ጥራ፤ ነቢዩና ባልደረቦቹ የሰሩትን ብቻ ስራ። አላህንም ምህረትና መመራትን ጠይቀው። ይህን ስጽፍ ድፍን አንድ ሰአት ወሰደብኝ🥲 ወ-ሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ።
Jul 24, 2023