ሰላም ✋ እኔ የምለው የኦሮሚያ ሲኖዶስ ሲመሰረት እና ጳጳሳት ሲሾሙ ከሁሉም ውግዘት እና ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር አርቲስቶች ታዋቂ ሰዎች ሳይቀሩ ጥቁር ለብሰው እዬዬ ሲሉ ነበር ሀዘንም ተቀምጠው ነበር የመንግስት አካላትንም በሀይማኖታችን አትግቡ ብለው ሲያስፈራሩ ነበር ዛሬ የትግራይ ቤተ ክህነት ሲቋቋም ግን ጥቁር የለበሰ እዬዬ ያለ የጮኸ የለም እንደውም እራሷ ሲኖዶስ መንግስት ጣልቃ ይግባልን ብላ መግለጫ ከመስጠት ውጪ ምንም ያደረገችው ነገር የለም እና ያኔ መንግስት አይመለከተውም አሉ ዛሬ መንግስት ያስቁምልን ? እንዴት ነው ነገሩ የፖለቲካ እና የጥቅም እንጂ የእምነት አይደለም ማለት ነው ? ይህ አስመሳይነት እና የፖለቲካ የሀይማኖት ንግድ መቼ ነው የሚቆመው ? በነገራችን ላይ 1. በትግራይ መንበረ ሰላማ መቋቋም በጣም ከተደሰቱት አንዱ ነኝ እንኳን ደስ አላችሁ 2. መንበረ ሰላማ አሁን ካለው መንበረ አክሱም ዘወጨጌ የሚቀድም ታሪካዊ ስያሜ ነው መንበረ ሰላማ በ4ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ስያሜ ነው መንበረ አክሱም ደግሞ በ13ተኛው ክፍለ ዘመን የመጣ ስያሜ ነው
Jul 22, 2023እኔም ባንተ ሃሳብ እስማማለሁ ሁሌም እነሱ ሚያለቅሱት ስለ ቤ/ክርስትያን ሳይሆን ስለ ብሄር ነዉ
Jul 24, 2023