I am 22 f.ive never been i rnship.guys have asked me to be their gf but i wana date for marriage so i declined their request .not bc i have some unrealistic expectations but bc i didn't have any feelings fr any of them...but nowadays i have this concern that i will never meet that someone .given that i am not that outgoing girl and i dont have the exposure to meet new ppl.so should i just date and and the attraction will come eventually or just wait fr ''the one''?
Jul 19, 2023ወንድ በመሆኔ ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በደንብ አንብቢሊኝ። ባለንበት ዘመን ስርአት ያላቸው የተከበርንና የተመሰገንን ወንዶች እንዳለን ሁሉ ብዙ ወንዶች ሴትን የምንፈልገው ጊዜያዊ ስሜታችንን ለመወጣት ነው። በመጀመሪያ ጥሩ ወንድ ቢኖር እንኳ ለእንዲህ አይነት ህይወት አዲስ በመሆኑ ጉዳዩን በትክክል handle አያደርገውም። ከቤተሰቦቹም ጥሩ የትዳር ህይወት ተሞክሮን አይቀስምም። በዚህም የተነሳ አሁን እየሰማን እያነበብንና እያየን ያለውን የፍቅር ህይወት ምስቅልቅል እንረዳለን። (ሴቶቹም እንደዛው!) ሲቀጥል ሁለተኛው አይነት ወንድ ምን አይነት ሰው መሰለሽ?.. ከመጀመሪያ የፍቅር አጋሩ ጋር በተለያዩ ምክንያቶች breakup ያደረገ በመሆኑ ሶስት አይነት ነው። 1, ያለፈቿን እያስታወሰ የወደፊቱን የማይኖር 2, ሴትን የሚጠላና ትዳርን የማያስብ ሴትን የማይቀርብ 3, ሴትን የሚጠላና ለመበቀል የተነሳ በዚህም ቀጣይ ህይወቱ ላይ ከሴት ጋር ያለው መስመር ተበላሽቶ ያቺንም ሁለተኛ ሴት መስመሯን ያበላሸዋል። ሶስተኛው ወንድ በተፈጥሮው ለሴት ጥላቻ የለውም። ነገር ግን የሴት ጥማት ያለበት ሁሌም በሴት እግሮች ታቅፎ ማደር የሚፈልገው ልፍስፍስ አይነት ወንድ ነው። ወጣት ወይም ቆንጆ ወይም ባለሃብት የሆነችን ሴት እያጠደመ የሚኖርም ነው። አንዳንዱ በጥላቻና ምቀኝነት ተነሳስቶ የሴትን ህይወት ሲያናጋ ሌላኛው የሴት ጥማት ስላለበት ብቻ የሴትን ህይወት ያናጋል። እንዲህ አይነት ወንዶች በበዙበት ዘመን ወደድኩሽ ብሎ የመጣን መቀበል ራስን ለእርድ ማዘጋጀት ነው። ጥሩ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች እጅግ የተመናመኑበት፣ ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ክብርና ልፋት ደንታ የሌላቸው ስለበዙ ነክሰው የሚሮጡ ውሾች በየቦታው ታያቸዋለሽ። ለትዳር የሚሆንሽን ሰው ከፈለግሽ ወደ ቤተ-እምነት መዞር ካሉ አማራጮች የተሻለው ነው። እዚያም ቢሆን ጥንቃቄ ይሻል። ወደ ቤተሰቦችሽም ብትዞሪ አይከፋም፤ የተሻለውን ወላጆቻችን ያውቁልናል። ከራሳቸው ስለተማሩ ለልጆቻቸው አርቀው ይመለከታሉ። በተሻለ መልኩ ማብራራት እችል ነበር። ከቤት ውጭ ስለሆንኩ መጻፍ የምችለውን ጽፌያለሁ። ተጨማሪ ሐሳብ ከፈለግሽ ውይይቱን እንቀጥላለን።
Jul 20, 2023