ብዙዎቻችን የሌሎችችን እምነት በቅጡ ሳናውቅ ለመውቀስ እንሮጣለን እናም የሌሎችን እምነት በተወሰነ ለማወቅ ስለፈለግሁ ነው? ስለራሳቹ እምነት የምታቁትን ንገሩኝ 1,ዋና አስተምሮ ምንድን ነው ? 2 ከሞት ብኋላ ያለውን ህይወት ለማግኘት ምን ላድረግ ? 3 አንዳንዶች በትአምር ያምናሉ (ስለዚ ያያችሁትን ) አጭር እና ግልጽ በሆነ መንገድ ብታቀርቡት ጥሩ ነው 🙏🏽 thanks in advance ለመሰዳብ እና ስለሌላው ለማውራት ከመጣህ እየሄድክ 🚶🏼♂️🚶🏼♂️
Jul 15, 2023በቅድሚያ Thank you for your open mindedness. 1. የኢስላም ዋናዉ አስተምህሮ በአሏህ አንድነት እና ብቸኛ ፈጣሪነት እና ተመላኪነትማመን እና ሙሀመድም የእርሱ የመጨረሻ ነብይነት ማመን ነዉ፡፡ ፈጣሪያችን አሏህ አልወለደም አልተወለደም አምሳያ እና ቢጤም የለውም፡፡ ሁሉንም ነገር የፈጠረው እና የሚያስተዳድረው ብቻዉን ነዉ ሊመለክ የሚገባዉም ብቻዉን ካለምንም ተጋሪ ነዉ፡፡ ክብሩ የላቀዉ ፈጣሪያችን አሏህ ህዝቦችን ለማስተማር እና ወደቀጥተኛዉ መንገድ ለመመምራት በየጊዜው ነብያትን የተለያየ ተአምራት ሰጥቶ ልኳል፡፡ ኖህ ሙሴ አብረሃም እየሱስ ሙሀመድ (ሠላም በሁሉም ላይ ይስፈን) ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡ ሁሉም የአሏህ ነብያት ናቸዉ የእርሱን አንድነት አስተምረዉ፤ ብቸኛ ተመላኪነቱን ሰብከዉ ፤ ተአምራትንም አሳይተዋል፡፡ ይህን ተአምር ማሳየታቸዉ ግን ከራሳቸው ሳይሆን ከፈጣሪያቸዉ የተሠጠ፤ እነርሱን ሳይሆን አምላካቸውን እንድናመልክ እና በእርሱም ላይ እምነታችን ይፀና ዘንድ እንጂ እነርሱን ወደ አምላክ ደረጃ ከፍ አርገን እንድናመልካቸዉ እና እንድንገዛቸዉ አይደለም፡፡ ሙሀመድ የነብያት መደምደሚያ ናቸዉ፡፡ 2.ኢስላም ከሞት በኋላ ስላለ ህይወት በሰፊው ያስተማረ ሀይማኖት ነዉ፡፡ ሁሉም ፍጡር ሟች ነዉ ፤ ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ይህ ምድር የስራ ቀጣዩ ደግሞ የምንዳ ሀገር ነዉ፡፡ በዚህ ምድር ስለሠራነዉ እያንዳንዱ ነገር አሏህ ፊት ቆመን እንጠየቅበታለን እንመነዳበታለንም፡፡ መልካም ከሠራን መልካም መጥፎ ከሰራንም የእጃችንን እናገኛለን፡፡ ማንም በድሎ ማንም ተበድሎ አይቀርም! ከሞት በኋላ ፍፁም ፍትሀዊው ፈራጅ ፈጣሪያችን አሏህ ፊት ቀርቦ ይዳኛል፡፡ አይደለም ሰዉ እንሰሳቱ ፍትህ ሳያገኙ አይቀሩም! አንዲት እንሰሳ ሌላዋን በቀንዷ ወግታት ከሆነ አሏህ ፊት ቀርበዉ ይዳኛሉ! የትኛውም ስራ እንዲሁ ባክኖ ተረስቶ አይቀርም፡፡ በፍጡራን መሀል ፍትህ ከሠፈነ በኋላ በአሏህ ያመኑ መልካምም የሠሩ ዘላለማዊ ደስታ ወደሚያገኙበት ሞት ወደሌለበት ወደ ጀነት በአሏህ የካዱ ወደ ዘላለማዊ የቅጣት ሀገር ጀሀነም ይሄዳሉ፡፡ 3.በተአምራት እናምናለን፡፡ በአሁን ዘመን ግን አንዳንዶች እንደሚሉት በየሠፈሩ የሚገኝ ሳይሆን እጅግ በጣም rare ነዉ
Jul 16, 2023