#religion
Hey guys besenbet men mendnew maderg yelelben detail negerogn Ena demo kesebet wechi abyt baloch mendnachew
Jul 14, 20231 engagements
Hey guys besenbet men mendnew maderg yelelben detail negerogn Ena demo kesebet wechi abyt baloch mendnachew
Jul 14, 2023ሰንበትን ቀድሷት እንዲል ቃሉ በሰንበት መልካም ነገሮችን ማድረግ አለብን። ከሁሉ የሚቀድመው በለሊት ሄደን ቅዳሴውን ሙሉ መሳተፍና ማስቀደስ ብንችል መቁረብ። ሰንበትን የሚያከብር ፃድቅ ነው ይላል ቅዳሴ መጽሐፉም። ከዚያም ደግሞ የታመመ ቢኖር መጎብኘት የታሰረ ቢኖር መጠየቅ መልካም ነው። ለምን በሌሎች ቀኖች አናደርግም ቢባል በሌሎችም ቀን ማድረግ አለብን ግን ሰበበኞች ስለሆንንና የዓለም ውጣ ውረድን ምክንያት ስለምናደርግ ሰንበትን ሰበብ እንዳይሆን ተሰጠን። አበይት በዓላት የሚባሉት ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማእታት፣ ቅዱሳን መላእክት እንዲሁም አምላካችን በተለያዩ ጊዜያት ያደረጉትን ተዓምራት የምንዘክርባቸው ቀናቶች ናቸው። እነዚህንም በዓላት በየወሩም እናስባቸዋለን። ከዚያም ግን መላእክት ለሆኑት ሁሉ ቅዱስ ሚካኤልን ለፃድቃን ሰማእታት ሰዎች ሁሉ እመቤታችንን ለአምላክ ደግሞ በዓለ እግዚአብሔርን ወክለን ማክበር አለብን። በዚያም ጊዜ ልክ እንደሰንበት መልካም በማድረግ የተራበን በማብላት የተጠማን በማጠጣት የታረዘንም በማልበስ ሰዎችንም በመርዳት በመልካም ግብር ማሳለፍ አለብን። 😊
Jul 18, 2023