Mj46
#relationships
ሰላም ሰዎች እንዴት ናችሁ እስቲ አማክሩኝ ከፍቅረኛዬ ጋር 9 ወር አከባቢ ሆኖናል። በጓደኝነት ደግሞ 2 አመት አብረን ቆይተናል። ቢሆንም የሁለት አለም ሰዎች ነን። እኔ መንፈሳዊ ህይወት እንዲኖርን እፈልጋለሁ እሱ ግን ዝግጁ አይደለም ንስሐ እንድንገባ ብጠይቀዉም እንቢ ነው መልሱ እንደሚወደኝ አልጠራጠርም እኔም ከልቤ እወደዋለሁ ግን አስተሳሰባችን ምንም ሊጣጣም አልቻለም እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ ስለምትወዱት ዝም ብላችሁ እሱ የሚለውን ታደርጋላቹ ወይስ የራሳቸውን መንገድ ትከተላላቹ? አመሰግናለሁ
Jul 14, 20234 engagements