Selam Passport lemawtat felge nbr gn mnm yemawkew ngr yelem pls step by step ngerugn priceunm chemr pls tebaberugn
Jul 11, 2023አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፦ የሚያስፈልጉት የልደት ምስክር ወረቀት እና የአገልግሎት ጊዜው ያላለቀ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ ሲሆኑ ምንም አይነት ተጨማሪ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡ የሚወስደው ጊዜ ከአንድ ወር በላይ ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ፓስፖርት #በአስቸኳይ ማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳዩን አስቸኳይነት የሚያሳዩ ማስረጃዎች ያስፈልጋሉ፦ ጉዳዩ የስራ ከሆነ ከመስሪያቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ እና የመስሪያ ቤቱ መታወቂያ የህክምና ወረቀት(ሪፈር) ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር መኖሪያ ፍቃድ ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር የስራ ፍቃድ የኢምባሲ ቀጠሮ ተመላላሽ መንገደኞች ሆነው ፓስፖርት ገፁ ያለቀባቸው ፓስፖርቱን ይዞ መቅረብ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ጊዜ ያለው የባህረኞች መታወቂያ (ሲማንቡክ) ሆነው የሁሉም አገልግሎቶች አከፋፈል ሁኔታ እንደአገልግሎቶ የተለያየ ነው፡፡ ለፓስፖርት እድሳት፦ የቀበሌ መታወቂያ እና ፓስፖርት ኮፒ የጠፋ ፓስፖርት፦ የቀበሌ መታወቂያ እና የፖሊስ ማስረጃ
Jul 11, 2023