ወደ አረብ ሀገር ከተሰደድኩ አመት ሊሆነኝ ነው። ግን ምንም ገንዘብም ሆነ አንዳች ነገር ላገኝ አልችልም ስታሰራኝ የነበረች ሴት ጎረምሳ ልጇ ማታ መቶ ሊደፍረኝ ሲታገል የሙት ሽረቴን ታግዬ ባስለቅቀውም ማዳም ጥፋተኛ እኔኑ አድርጋ ደሞዜን ሳትከፍለኝ አባረረችኝ። ረዳቸዋለው ብዬ ከሀገር የወጣውት አቅሙ ከድቶት ከዘራ የተደገፈው አባቴ ሀገርቤት እያለው ሻይ ቡና ስሰራ ጀምሮ ሚያየው የኔን እጅ ነው።ዘመድ ሁላ ፊቱን አዙሮብኛል ያለኝ ብቸኛ አማራጭ ገላዬን መሸጥ እንደሆነ እዚ ያገኘዋቸው ሁላ እያሉኝ ነው።ምን ላድርግ? ቤተሰቦቼ እንኳ እህል ቀምሰው ሚያድሩት በልጅነት የሰፈር ጓደኛዬ ከቤት እንዲማር በሚላክለት ብር ምክንያት ነው...ምን ትመክሩኛላቹ? መርዳት ምትችሉም እህታቹን አድኑኝ
Jul 05, 2023በጣም ከባድ ነው ግን እንደዚህ አይነት ውሳኔ ከመወሰንሽ በፊት ሌላ አማራጮችን ሞክሪ ።
Jul 06, 2023