ሰላም እንዴት ናችሁ ዛሬ አንድ ነገር ላማክራችሀ መጥቻለው። አቃለው እስካሁን የብዙ ሰው ስሜት ስትጋሩ ቆይታችኋል።እኔም ዛሬ እርዳታችሁን እፈልጋለሁ። ፍቀረኛ አለኝ። አሁን ላይ ተራርቀን ነው የምንኖረው።በፊት ላይ በጣም ይንከባከበኝ፣ያስብልኝ፣ እንደሚወደኝ እና እንደሚያፈቅረኝ ሁሌ ይነግረኝ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ ጭራሽ ሰለኔ ማሰብ አቁሟል። አይደውልም ሳናወራ ለረዥም ጊዜ እንቆያለን ፣ ሁሌ እጣላለን በፊት ተኮራርፈን የማናውቅ ሰዎች እንደተዘጋጋን ቀናቶች ተቆጠሩ።ባህሪህ ተለውጧል አስተካክል ብዬ ብዙ ጊዜ ነግሬው ነበር ነገር ግን እስካሁን ምንም ለውጥ የለውም። እኔ ደግሞ በፊትም አሁንም አፈቅረዋለው።ሳላለቅስ ያደርኩበት ቀን የለም።እየተጎዳሁ ነው። እሱን ማጣት ለኔ ሞት ነው። ከምታስቡት በላይ ተላምጄዋለው።በዙሪያዬ በጣም ብዙ ጓደኞች አሉኝ ግን ለአንዳቸውም የውስጤን አውጥቼ መናገር አልቻልኩም። ምክንያቱም አይረዱኝም። እባካችሁ እናንተ በኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታረጉ ነበር? ባትመልሱልኝ እንኳን የውሰጤን አወጥቼ ስለነገርኳችሁ ቀለል ብሎኛል። ለምትመልሱልኝም አመሰግናለሁ❤️❤️
Jul 04, 2023በኔ ምልከታ እንደዚህ አይነት ነገሮች ሊፈጠሩ የሚችሉት 1. በሆነ ነገር ደብሮት ከሆነ 2. ምን አልባት አስቀይመሽው ከሆነ 3. በሌላ ሴት ተስቦ ከሆነ ግንኙነታቹ ስልችቶታል ማለት ነው ። እኔ ምመክርሽ ከላይ ያስቀመጥኩልሽን ምክንያቶች እና የራስሽን ምክንያቶች አንድ ላይ አርገሽ በግልፅ ብትጠይቂው የተሻለ ነው ። ሌላው ደግሞ በራስ መተማንሽን ከፍ ማድረግ አለብሽ። ምን አልባት ከሌላ ሴት ጋር ጀምሮ ከሆነ መለያየታቹ ስለማይቀር እራስሽን ማዘጋጀት አለብሽ። ዋናው መፍትሄ ችግሩን በግልፅ መጠየቅ እና መነጋገር ነው ። እንዲታ በላይ በላይ ሳይሆን ሰፊ ጊዜ ወስደሽ በዝርዝር አናግሪው።
Jul 05, 2023