ሰላም። ራሳችሁን ከቻላችሁ በኋላ ወይም መወሰን በምትችሉበት እድሜ ሃይማኖታችሁን የቀየራችሁ ሰዎች የቀየራችሁበትን ምክንያትና አጋጣሚ ንገሩን?
Jun 30, 2023ለብዙ ጊዜያት የፕሮቴስታንት አማኝ ነበርኩ በጣም አክራሪ። እና ኦርቶዶክስ በሙሉ ሁሌ ያሳዝኑኝ ነበር። ግን የሆነ እንደ ቀልድ እስኪ ከነሱ ጋር ያለውንም ነገር መስማት አይከፋም። ባይጠቅምም አይጎዳኝም ብዬ ንባብ እና መረዳት ላይ ገባው። 4 አመት ከራሴ ጋ እየታገልኩ አጠናው በመጨረሻ መሃይም እንደነበርኩ ተረዳው። አፈርኩ በራሴ። የእስከዛሬው እምነቴ ልክ እንደ ጉም የዘገንኩት እንጂ የተጨበጠ እንዳልሆነ ገባኝ። መጀመሪያ ቤተመቅደስ ውስጥ የገባሁበትን ጊዜ አረሳውም። ገነትን ምድር ያየሁት ነበር የመሰለኝ። አምልኮ እንዲ እንደሆነ የገባኝ ያኔ ነው። ዛሬ ግን በድፍረት እላለው ክብር ለድንግል ማርያም ልጅ ይሁን። ከትእቢት ወደ ትህትና ከመታበይ ራስን ዝቅ ወደማረግ ከመለፍለግ ወደ ዝግታ ከዝላይ ወደ ጾምና ስግደት መልሶኛል። ያለፉትን አመታት ሳስባቸው አሁን ላይ ትንሽ ፈገግ ያስብሉኛል😊
Jun 30, 2023