ሰላም ሰወች! በጣም እያስጨነቀኝ ያለ ነገር ላካፍላችሁ እና እባካችሁ ሀሳብ አትንፈጉኝ፤ የክፍለሀገር ልጅ ነኝ እና ከሴት ጓደኛዬ ጋር almost 4 አመት እየሞላን ነው እና በጣም ነው የምንዋደደዉ ግን አሁን በመሃላችን ትልቅ ነገር ተከስቷል እሱም እንደነገርኳችሁ የክፍለሀገር ልጅ ነኝ እና አከባብያችን ለይ ብዙ ጎሳዎች አሉ ከነዚያም ዉስጥ አንዱ ጎሳ እንደ የበታች ስለሚቆጠር አብዛኛውን ግዜ ሌሎቹ ጎሳዎች ከዚያ ጎሳ አያገቡም እና እንዳለመታደል የኔም gf ከዚያ ነች እና እኔ ደሞ ከሌላው ነኝ ይህንንም ያወኩት ከ3 ሳምንት በፊት ነበር እና ግን አሁንም በጣም አፈቅራታለዉ እሷን ምትተካ ሴት ያለችም አይመስለኝም ግን ይሄን ነገር ምን ላርግ የሆነ ግዜ በንደዚሁ አይነት ጉዳይ አንዱ የሆነችዋን አግብቶ ጎሳዉ ተሰባስበው ረግመዉት አመት ሳይሞላ ሞተ እኔ አሁን የምፈራው ተረግሜ መሞትን አደለም ግን እናቴን ነው ያለ አባት ነው ያሳደገችኝ ለዚህ ነገር ደሞ እሷም ጥሩ አመለካከት የላትም እንደ ቀልድ እንኳ ከዚያ ጎሳ ባገባስ ብዬ ብጠይቃት በጣም አክርራ ነው ምትመልስልኝ እኔም ደሞ እሷን ማስከፋት አልፈልግም በሌላ በኩል ደሞ ፍቅረኛዬን ለማጣት በምኔም ዝግጁ አደለሁም፥ብችል እንኳ እንደዚህ ተናግርያት ልቧንም ሞራሏንም መስበር አልፈልግም ግን እሺ ምን አርግ ትሉኛላችሁ??? እባካችሁ ዝም ብላችሁ አትለፉ🙏(ነገሩ አሁን እንደነገርኳችሁ ቀላል አደለም)
Jun 26, 2023Yooo, gosa mnamn mibal ngr yelm endi aynt ngr ayseram lendzi aynt mkniat blh endatatat kasfelge yezhat tefa
Jun 27, 2023